From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ችግር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከሙላትህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
ጭንቀት ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከሰላምህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
ድካም ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከጉልበትህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
ማጣት ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከዙፋንህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም
ይሟሟሉ ፡ ይቀልጣሉ ፡ መገኘትህን ፡ ሲረዱ
የከበዱት ፡ ዙፋን ፡ ስጡኝ ፡ ያሉ
ለቀው ፡ ሄዱ ፡ እያፈሩ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ (፬x)
ከተራራው ፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከከበደው ፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከነገሩኝ ፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከችግሩ ፡ በላይ ፡ ትልቅ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ትልቅ (፬x)
ከጨነቀኝ ፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከነገሩኝ ፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከሰበክነው ፡ በላይ ፡ ትልቅ
ካመለኩት ፡ በላይ ፡ ትልቅ
የሰልፉ ፡ አለቃ ፡ ብቻህን ፡ ምትገዛ
ምድርን ፡ ፍጥረትን ፡ በቃልህ ፡ ያጸናህ (፪x)
ዕድሜ ፡ ማይወጣልህ ፡ ኃይልህ ፡ አይለካ
ምሽግ ፡ መጠለያ ፡ ክንድህ ፡ የበረታ (፪x)
ገብተህ ፡ በእኔ ፡ ጓዳ (፪x)
ኧረ ፡ ለምን ፡ ልፍራ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ትልቅ ፡ (፬)
ከጨነቀኝ ፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከነገሩኝ ፡ በላይ ፡ ትልቅ
ከሰበክነው ፡ በላይ ፡ ትልቅ
ካመለኩት ፡ በላይ ፡ ትልቅ
|