ትንሳዔውን ፡ ተናገሩ (Tensaewen Tenageru) - ሄኖክ ፡ አዲስ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሄኖክ ፡ አዲስ
(Henok Addis)


(1)

ልኑር ፡ በቤትህ
(Lenur Bebieteh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:52
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሄኖክ ፡ አዲስ ፡ አልበሞች
(Albums by Henok Addis)

አበቃለት ፡ ተብሎ ፡ ነበር ፡ ኢየሱሴ ፡ ሲቀበር
ወሬ ፡ ሆኖ ፡ ሊቀር
አለፈ ፡ ተብሎ ፡ ቢወራ ፡ ነበር ፡ ተብሎ ፡ ሊዘከር
ወሬ ፡ ሆኖ ፡ ሊቀር
የዓለምን ፡ ታሪክ ፡ ለወጠ ፡ ነገር ፡ ተገለበጠ
የአዳም ፡ ዘር ፡ አመለጠ
መቃብሩን ፡ ፈነቃቅሎ ፡ ሰይጣንን ፡ ጉድ ፡ አረገ
ወደ ፡ አባቱ ፡ አረገ

የሰው ፡ኃጢአት ፡ ተወገደ ፡ ተሻረ ፡ የእኛ ፡ አበሳ
በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ
መቼ ፡ እንደሞተ ፡ ቀረ ፡ ከሙታንም ፡ ተነሳ
በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ

ኢየሱስ ፡ ተነሳ
ጌታዬ ፡ ተነሳ (፪x)

ትንሳዔውን ፡ ተናገሩ ፡ የእምነት ፡ አባቶች ፡ መሰከሩ
እኔም ፡ ለትውልድ ፡ ልናገርው
ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ፡ ልመስክረው (፪x)

ተነስቷል ፡ ይሄ ፡ ጌታ
ማኅተሙን ፡ እርሱ ፡ ፈታ
ቅዱሳን ፡ በአንድ ፡ ሁኑና
አክብሩት ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)

ዕልልታ ፡ ሙገሳ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ ለነሳ
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነስቷል ፡ አክብሩት ፡ ቅዱሳን
የታል ፡ ዕልልታ ፡ ለአዳነን ፡ ጌታ
የታል ፡ ጭብጨባ ፡ መቅደስ ፡ የሚገባ (፪x)

ኃይል ፡ እንደሌለው ፡ ቢመታ ፡ ወደ ፡ መስቀል ፡ ቢነዳ
በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ
በእንጨት ፡ ላይ ፡ ቢንጠለጠል ፡ ስለ ፡ ሰው ፡ ልጅ ፡ ቢጐዳ
በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ
ቢያሾፉ ፡ ቢያሳልቁበት ፡ እያሉ ፡ በል ፡ ውረዳ
በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ
በደሙ ፡ እርቅ ፡ አወረደ ፡ አፈረሰ ፡ ያን ፡ ግድግዳ
በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ
ኢየሱስ ፡ ተነሳ ፡ ጌታየ ፡ ተነሳ(፪×)

ትንሳዔውን ፡ ተናገሩ ፡ የእምነት ፡ አባቶች ፡ መሰከሩ
እኔም ፡ ለትውልድ ፡ ልናገርው
ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ፡ ልመስክረው (፪x)

ተነስቷል ፡ ይሄ ፡ ጌታ
ማኅተሙን ፡ እርሱ ፡ ፈታ
ቅዱሳን ፡ በአንድ ፡ ሁኑና
አክብሩት ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)

ዕልልታ ፡ ሙገሳ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ ለነሳ
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነስቷል ፡ አክብሩት ፡ ቅዱሳን
የታል ፡ ዕልልታ ፡ ለአዳነን ፡ ጌታ
የታል ፡ ጭብጨባ ፡ መቅደሱ ፡ የሚገባ (፪x)