እኔ አልፈራልም (Enie Alferam) - ሄኖክ ፡ አዲስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሄኖክ ፡ አዲስ
(Henok Addis)

Henok Addis 1.jpg


(1)

ልኑር ፡ በቤትህ
(Lenur Bebieteh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:52
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሄኖክ ፡ አዲስ ፡ አልበሞች
(Albums by Henok Addis)

በልዑል መጠጊያ ሁሉን በሚችለው
ተማምሬ አድራለሁ ከለላዬ እርሱ ነው
እኔ አልፈራም እሱን ይዤው
እኔ አልፈራም ተደግፌው

ትናንትናን ደርሶ አድኖኝ ዛሬን እንዴት እፈራለሁ
የክንዱን የሃይሉን ብርታት በአይኖቼ አይቻለሁ
እንዳልፈራ እንዳልሸበር ስሙ ለኔ ዋስ ሆኖኛል
የከበረው የጌታ ስም ጠላቶቼን መቶልኛል


ለምስኪኑ መታመኛ ለደሃ አደግ የሚራራ
ፅኑ አለት ድንቅ ጌታ ኢየሱስ ነው መደገፊያ
በአንዳች እንኳን እንዳልፈራ ድንቅ ታምር እየሰራ
ህይወቴ ሁሉ እርሱ ገዝቶ አኑሮኛል እየመራ

ሸንበቆን አይደለም እኔ የተደገፍኩት
ድንገት የሚሰበር መች ሆነ የያዝኩት
አስተማማኝ ምርኩዝ ተፈትኖ የፀና
የማዕዘኑ ራስ ድጋፌ ነውማ

አሃሃ ተደግፌሃለሁ
አሃሃ ተማምኜሃለሁ
አሃሃ በአስተማማኝ ክንድህ
አሃሃ እኔስ አርፌአለሁ