የእግዚኣብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ (YeEgziabhier Lej Eyesus) - ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

(፬x)

ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር
(Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

Harar Amanuel Menfesawi Maheber 1.png


(1)

እግዚኣብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው
(Egziabhier Tewagi New)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር ፡ አልበሞች
(Albums by Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

የእግዚኣብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ በሰማያት ፡ በክብር ፡ ያለኸው
አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ የሚገባው (፪x)

ክብሩ ፡ ከሰማያት ፡ በላይ ፡ ነው
እንደ ፡ አምላኬ ፡ እንደ ፡ እግዚኣብሔር
ኧረ ፡ ከቶ ፡ ማነው (፪x)

እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ(፬x)

በማን ፡ ትመሰላለህ
ከማንስ ፡ ጋር ፡ ትስተያያለህ (፪x)

ውሆችን ፡ በእፍኝህ ፡ የሠፈርክ
ሰማይን ፡ በሥንዝርህ ፡ የለካህ
እግዚኣብሔር ፡ አንተ ፡ እግዚኣብሔር ፡ ነህ
እግዚኣብሔር ፡ አንተ ፡ ግሩም ፡ ነህ


ከእልፍ ፡ የተመረጥክ ፡ ውበትህ ፡ ያማረ
ከምንም ፡ ከማንም ፡ እጅግ ፡ የከበረ
በሞገስ ፡ በግርማ ፡ በክብርም ፡ ያለህ
የአማልክት ፡ አምላክ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)

በምሥጋና ፡ ልቀህ ፡ ታይ ፡ ጌታ (፬x)
ሃሌሉያ (፲x)
ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ (፬x)