ውለታህ (Weletah) - ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር
(Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

Harar Amanuel Menfesawi Maheber 1.png


(1)

እግዚኣብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው
(Egziabhier Tewagi New)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር ፡ አልበሞች
(Albums by Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

ውለታህ ፡ ውለታህ
ከአዕምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ነው ፡ አሃሃ (፫x)

ጌታዬ ፡ ውለታህ ፡ ከአዕምሮዬ ፡ በላይ
ኢየሱስ ፡ ውለታህ ፡ ከአዕምሮዬ ፡ በላይ (፪x)

ታላቅ ፡ ምሬቴ ፡ ለመልካም ፡ ሆነ
በአንተ ፡ ታሰብኩኝ ፡ ጭንቀቴ ፡ ቀረ
በጉብኝትህ ፡ ደስ ፡ አሰኘኸኝ
ታላቅን ፡ ነገር ፡ አደረግህልኝ (፪x)

አባቴ ፡ መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ ለኔ ፡ አድርግ
ጌታዬ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ድንቅን ፡ ለእኔ ፡ ሠርተሃል
እግዚኣብሔር ፡ ጻድቅ ፡ ነህ ፡ በጽድቅ ፡ መርተኸኛል
እንዳለ ፡ ግን ፡ በሕይወት ፡ መኖርን ፡ ሰጥተኸኛልና

ታዲያ ፡ ለዚህ ፡ ለውለታህ ፡ ምን ፡ እከፍልሃለሁ (፪x)
ባይመጥንም ፡ ምሥጋናዬ ፡ ሃሌሉያ ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ (፪x)
ለውለታህ ፡ ጌታ ፡ የምከፍልህ ፡ አጣሁ
ለስጦታህ ፡ ኢየሱስ ፡ የምሰጥህ ፡ አጣሁ
(፪x)

ባከባብርህ ፡ ይሄ ፡ አይበቃህም
ባሞጋግስህ ፡ ይሄ ፡ አይበቃህም

ተመስገን ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ተመስገን ፡ ነው ፡ ያለኝ
ተባረክ ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ተባረክ ፡ ነው ፡ ያለኝ
(፪x)
ቃላቶች ፡ ያጥሩኛል ፡ ለውለታህ ፡ ምላሽ
ኧረ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ነህ ፡ ደራሽ (፬x)