ምንጩ ፡ ፈለቀ (Menchu Feleqe) - ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር
(Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

Harar Amanuel Menfesawi Maheber 1.png


(1)

እግዚኣብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው
(Egziabhier Tewagi New)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር ፡ አልበሞች
(Albums by Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

ፍቅሩ ፡ የማይለወጥ ፡ የሚራራ ፡ አሃሃ
ምሕረቱ ፡ የበዛ ፡ ጌታ
ፍቅሩ ፡ የማይለወጥ ፡ ምሕረቱ ፡ የበዛ ፡ አሃሃ
እንደ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ቢፈለግም ፡ ጠፋ (፪x)
እንደ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሃሌሉያ ፡ ቢፈለግም ፡ ጠፋ

ቢፈለግም ፡ ቢፈለግም ፡ ጠፋ
(እንደ ፡ ጌታ) ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ቢፈለግም ፡ ጠፋ
(እንደ ፡ ኢየሱስ) ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ቢፈለግም ፡ ጠፋ
(እንደ ፡ ጌታ) ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ቢፈለግም ፡ ጠፋ

እንዳንተ ፡ ጌታ ፡ ብርቱ
እንዳንተ ፡ ብርቱ ፡ ኃያል
እንዳንተ ፡ ኃያል ፡ ኢየሱስ
ቢፈለግም ፡ ጠፋ (፪x)

ጊዜ ፡ አይቶ ፡ አይለወጥም
ፍቅሩ ፡ ወረት ፡ የለበትም
ዘለዓለም ፡ እርሱ ፡ እርሱ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ አፍቃሪ ፡ ነው

ሲወድም ፡ ምክንያት ፡ የለው
እንዲሁ ፡ አንዲሁ ፡ ነው
ዓለምን ፡ ሁሉ ፡ ወዶ
አዳነን ፡ ተአምር ፡ ሰርቶ

እግዚአብሔር ፡ እርህሩህ ፡ አምላክ
እግዚአብሔር ፡ ፃድቅ ፡ ነህ ፡ አምላክ
እግዚአብሔር ፡ እርህሩህ ፡ አባት
እግዚአብሔር ፡ ፃድቅ ፡ ነህ ፡ አምላክ

በምክርህ ፡ ቢሆን ፡ የምትደነቅ
በአገዛዝህ ፡ ከሁሉ ፡ የምትልቅ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ትልቅ
ፈልጌያለሁኝ ፡ አላገኘሁም
እንዳንተ ፡ የሚሆን ፡ ጌታ ፡ ከቶ ፡ አላየሁም

ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ እግዚአብሔር
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ ኢየሱስ
ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ እግዚአብሔር
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ ኢየሱስ

ምህረትህ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ጌታ
ምህረትህ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
ይቅርታህ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ጌታ
ይቅርታህ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
ጌታዬ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል ፡ አሃ
በምሕረት ፡ በቸርነት ፡ የተሞላ
(፪x)

ምህረቱን ፡ አበዛልኝ ፡ ለእኔ
ጌታዬ ፡ ስለወደደኝ ፡ አዳነኝ
(፪x)
እናገራለሁ ፡ ደግሞ ፡ አወራለሁ
ስለ ፡ ምሕረቱ ፡ ስለ ፡ ቸርነቱ
እናገራለሁ ፡ ደግሞ ፡ አወራለሁ
ስለ ፡ ርህራሄው ፡ ስለ ፡ ደግነቱ
አያልቅምና ፡ ከቁጥር ፡ በዝቶብኛል
እንዲሁ ፡ ብቻ ፡ እዘምራለሁ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ የለም ፡ እላለሁ
(፪x)

ውበትህ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ፍቅርህም ፡ ግሩም ፡ ነው
አሰራርህ ፡ አሰራርህ ፡ አሰራርህ ፡ የሚወደድ ፡ ነው
ቀና ፡ ብዬ ፡ ወደ ፡ ሠማይ ፡ ዞር ፡ ብዬ ፡ ዙሪያዬን ፡ ሳይ
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አጣሁልህ ፡ መሳይ (፪x)

ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ሃሌሉያ ፡ ለእኔ ፡ ሃሌሉያ ፡ በዘመኔ
(፪x)
ጨለማዬ ፡ በራ ፡ ብርሃን ፡ ወጣልኝ
በልቤ ፡ አየሁት ፡ ጌታዬን ፡ አወቅሁት
ምን ፡ ዓይነት ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ የማመልከው
በጨለማ ፡ ይብራ ፡ ብርሃንን ፡ ያለው

አለቆች ፡ የቆፈሩት ፡ አዛውንቶች ፡ የማሱት
ነቢያት ፡ ብዙ ፡ ያሉለት ፡ ምንጩ ፡ ፈለቀ (፮x)
ምንጩ ፡ ፈለቀ (፪x)