እሰዋለሁ (Esewalehu) - ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር
(Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

Harar Amanuel Menfesawi Maheber 1.png


(1)

እግዚኣብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው
(Egziabhier Tewagi New)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር ፡ አልበሞች
(Albums by Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

በጉባኤ ፡ መካከል ፡ ስእለቴን ፡ እፈፅማለሁ
ሥራህንም ፡ እያየሁ ፡ እኔ ፡ እደነቃለሁ (፪x)

በሥራህ ፡ አንተ ፡ ፍፁም ፡ አምላክ ፡ ነህ
አትሳሳትም ፡ ሁሌ ፡ እውነት ፡ ነህ
አንተ ፡ ብቻህን ፡ ሁሉን ፡ ሰርተሃል
በሥራህ ፡ እኩያ ፡ ታጥቶልሃል (፪x)

ማስተዋልህ ፡ ጥበብህ
አይመረመር ፡ ዕውቀትህ
አስተዋይ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
እውነተኛ ፡ ነህ ፡ አምላኬ (፪x)

ሥራህ ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው
ሥራህ ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው
አቤቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ አመሰግንሃለሁ (፪x)

ሁልጊዜ ፡ ክብርህንና ፡ ግርማህን ፡ እዘምረዋለሁ
ለዘለዓለም ፡ ያረግኸውን ፡ ሁሉ ፡ ለትውልድ ፡ እናገራለሁ (፪x)

ሠማይና ፡ ምድርን ፡ ሞልተሃል
እግዚአብሔር ፡ ማን ፡ ይመስልሃል (፪x)

ማንንም ፡ አትፈራም ፡ ሁሉ ፡ ይፈሩሃል
እግዚአብሔር ፡ አንተን ፡ ማን ፡ ይቋቋምሃል (፪x)

ከማውቅህ ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
የእኔ ፡ ቃል ፡ አንተን ፡ አይገልፅህ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ በከፍታ ፡ ድንቅ ፡ ነህ
የእኛ ፡ ጌታ ፡ በከፍታ ፡ ድንቅ ፡ ነህ
ድንቅ ፡ ነህ ፣ ድንቅ ፡ ነህ (፪x)

በመቅደስህ ፡ ድንቅ ፡ ነህ
በማደሪያህ ፡ ድንቅ ፡ ነህ
በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፣ ድንቅ ፡ ነህ (፪x)

ይሄ ፡ ድንቅነትህ ፡ አስገርሞኛል (፪x)
ምሥጋና ፡ እንድሰዋ ፡ አስገድዶኛል (፪x)

እሰዋለሁ ፡ አልሰለችም ፡ እሰዋለሁ
እሰዋለሁ ፡ አልታክትም ፡ እሰዋለሁ
እሰዋለሁ ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ እሰዋለሁ
እሰዋለሁ ፡ ለዘለዓለም ፡ እሰዋለሁ (፪x)