From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እግዚኣብሔር ፡ ብርሃኔና ፡ መድሃኒቴ ፡ ነው (፬x)
የሚያስፈራኝ ፡ ከቶ ፡ ማነው (፰x)
እግዚኣብሔር ፡ የሕይወቴ ፡ መታመኛዋ ፡ ነው (፬x)
የሚያስደነግጠኝ ፡ ማነው (፰x)
በረታለሁ ፡ ልቤን ፡ አጸናለሁ
እግዚአብሔርን ፡ ተስፋ ፡ አደርጋለሁ(፪x)
እግዚኣብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው (፫x)
ሥሙም ፡ እግዚኣብሔር ፡ ነው (፪x)
ቁጣውን ፡ ሰደደ ፡ ጠላቶቼን ፡ በላ
በአፍንጫው ፡ እስትንፋስ ፡ ውሆችን ፡ ከመረ
ፈሳሾችም ፡ ደግሞ ፡ እንደ ፡ ክምር ፡ ቆሙ
ጠላቶቼን ፡ ሁሉ ፡ አሳድጄ ፡ ይዣለሁ
ምርኮን ፡ ተካፍዬ ፡ ነፍሴን ፡ አጥግቤያለሁ (፪x)
አሃሃ (፬x)
በክብር ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ጊዜ ፡ ብሏል (፪x)
ፈረስ ፡ ፈረሰኛውን ፡ ከባሕር ፡ ውስጥ ፡ ጥሏል
እግዚአብሔር ፡ ጉልበቴ ፡ ዝማሬዬ ፡ ሆኗል
ይሄ ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ አመልከዋለሁ
የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ከፍ ፡ አደርገዋለሁ (፪x)
አሃሃ (፬x)
አቤቱ ፡ ቀኚ ፡ በኃይል ፡ ከበረ (፪x)
አቤቱ ፡ ቀኚ ፡ በኃይል ፡ ከበረ (፪x)
ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ መታ ፡ አደቀቀ
ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ መታ ፡ አደቀቀ (፪x)
አቤቱ ፡ በአማልክት ፡ መካከል ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው (፬x)
በምሥጋና ፡ የተፈራ ፡ ድንቅን ፡ ነገር ፡ የምታደርግ
በቅድስና ፡ የከበረ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው ፡ በዕርግጥ (፪x)
ቀኝህን ፡ ዘረጋህ ፡ ምድር ፡ ዋጠቻቸው
ጠላቶች ፡ አለቁ ፡ ኃይልህ ፡ አቃታቸው
በቸርነት ፡ ብዛት ፡ ሕዝብህን ፡ መራኸው
ወደ ፡ ቅዱስ ፡ መቅደስ ፡ በኃይል ፡ አስገባኸው
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው? (፬x)
|