ብሩክ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ (Beruk Semeh Yebarek) - ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር
(Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

Harar Amanuel Menfesawi Maheber 1.png


(1)

እግዚኣብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው
(Egziabhier Tewagi New)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 7:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር ፡ አልበሞች
(Albums by Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

አቤቱ ፡ አቤት ፡ አቤቱ ፡ አቤት
አንተ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አንተ
ለትውልድ ፡ ሁሉ ፡ መጠጊያ ፡ ሆነህ (፪x)

ተራሮች ፡ ሳይወለዱ ፡ ምድርም ፡ ሳይሠራ
ዓለማት ፡ ሳይፈጠሩ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ተራሮች ፡ ሳይወለዱ ፡ ምድርም ፡ ሳይሠራ
ዓለማት ፡ ሳይፈጠሩ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ

ሺህ ፡ ዓመት ፡ በፊትህ ፡ እንዳለፈች ፡ እንደ ፡ ትናንት ፡ ቀን
እንደ ፡ ሌሊትም ፡ ትጋት ፡ ነውና (፪x)

ዘመናትም ፡ የተናቁ ፡ ይሆናሉ
በማለዳ ፡ እንደ ፡ ሣር ፡ ያልፋሉ
ማልዶ ፡ ያብባል ፡ ያልፋል
በሠርክም ፡ ጠውልጎና ፡ ደርቆ ፡ ይወድቃል
(፪x)

አቤቱ ፡ አንተ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ዕውነትህም ፡ ይከብብሃል (፪x)
የባሕርንም ፡ ኃይል ፡ አንተ ፡ ትገዛለህ (፪x)
የሞገዱንም ፡ መናወጥ ፡ አንተ ፡ ዝም ፡ ታሰኘዋለህ
የሞገዱንም ፡ መናወጥ ፡ አንተ ፡ ዝም ፡ ታሰኘዋለህ

አቤቱ ፡ ከአማልክት ፡ የሚመስልህ ፡ የለም
እንደ ፡ ሥራህም ፡ ያለ ፡ የለም (፬x)
አቤቱ ፡ ከአማልክት ፡ የሚመስልህ ፡ የለም
እንደ ፡ ሥራህም ፡ ያለ ፡ የለም (፬x)

ያደረካቸው ፡ አሕዛብ ፡ ሁሉ ፡ ይመጣሉ
አቤቱ ፡ በፊትህም ፡ ይሰግዳሉ ፡ ሥምህን ፡ ያከብራሉ
አቤቱ ፡ በፊትህም ፡ ይሰግዳሉ ፡ ሥምህን ፡ (ያከብራሉ)

አቤቱ ፡ ድንቅን ፡ የምታደርግ ፡ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህና
አንተ ፡ ብቻህን ፡ ታላቅ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነህና (፪x)

አምላክ ፡ ሆይ ፡ ዙፋንህ ፡ እስከ ፡ ዘላለም ፡ ድረስ
ይኖራል ፡ ይኖራል
የመንግሥትህ ፡ በትር ፡ የቅንነት ፡ በትር ፡ ነው (፬x)

በበረከትና ፡ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ ፡ ብሩክ ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፬x)
በበረከትና ፡ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ ፡ ብሩክ ፡ ስምህ ፡ ይባረክ (፬x)

ከሥም ፡ በላይ ፡ ሥም ፡ ይዘሃል
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል
ማን ፡ ይመስልሃል (፪x)

የፀና ፡ ብርቱ ፡ ግንብ ፡ ነው
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ኃይል ፡ አለው
የፃድቃን ፡ መክበሪያ ፡ ማምለጫ ፡ ዓለት ፡ ነው
ሥምህ ፡ ጉልበት ፡ ነው

የፀና ፡ ብርቱ ፡ ግንብ ፡ ነው
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ኃይል ፡ አለው
የፃድቃን ፡ መክበሪያ
ማምለጫ ፡ ዓለት ፡ ነው ፡ ሥምህ ፡ ጉልበት ፡ ነው (፭x)