አዋጅ ፡ ይነገር (Awaj Yeneger) - ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር
(Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

Harar Amanuel Menfesawi Maheber 1.png


(1)

እግዚኣብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው
(Egziabhier Tewagi New)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር ፡ አልበሞች
(Albums by Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

ውበቴን ፡ ንጉሥ ፡ ወዶ ፡ ማደሪያው ፡ አደረገኝ
በከበረው ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ በቀኙ ፡ አስቀመጠኝ
እርሱ ፡ በሚኖርበት ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ እንድኖር
ይኸው ፡ ተቀብሎኛል ፡ ጌታ ፡ እኔንም ፡ በክብር

አዋጅ ፡ ይነገር ፡ አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)
ንጉሥ ፡ ለወደደው ፡ እንዲህ ፡ ተደረገ
ንጉሥ ፡ ለሚወደው ፡ እንዲህ ፡ ተደረገ
እጅግ ፡ ባማረ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ እኖራለሁ ፡ በሠማይ (፪x)
አዋጅ ፡ ይነገር ፡ አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)

በዚህች ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በሥልጣን ፡ እንድኖር
በአሕዛብ ፡ ፈርጄ ፡ አለቆችን ፡ እንዳስር
ለእኔ ፡ ይህንን ፡ ክብር ፡ ጌታዬ ፡ አስረክቦኛል
ልጄ ፡ ወራሽ ፡ ነህ ፡ ብሎ ፡ ሁሉን ፡ በእጄ ፡ ሰጥቶኛል

አዋጅ ፡ ይነገር ፡ አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)
ንጉሥ ፡ ለወደደው ፡ እንዲህ ፡ ተደረገ
ንጉሥ ፡ ለሚወደው ፡ እንዲህ ፡ ተደረገ
በፍጥረታት ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ተሾምኩኝ ፡ ሆኜ ፡ የበላይ (፪x)
አዋጅ ፡ ይነገር ፡ አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)

ጠላት ፡ ባይገምትም ፡ እዚህ ፡ ይደርሳል ፡ ብሎ
የሃሳቤ ፡ ሳይሞላ ፡ እንድቀጠፍ ፡ በቶሎ
ግን ፡ በጌታዬ ፡ ልብ ፡ ውስጥ ፡ ስፍራ ፡ አገኘሁና
አብሬው ፡ ይኸው ፡ ቆምኩኝ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ነገስኩና

አዋጅ ፡ ይነገር ፡ አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)
ንጉሥ ፡ ለወደደው ፡ እንዲህ ፡ ተደረገ
ንጉሥ ፡ ለሚወደው ፡ እንዲህ ፡ ተደረገ
በፍጥረታት ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ነገስኩኝ ፡ ሆኜ ፡ የበላይ (፪x)
አዋጅ ፡ ይነገር ፡ አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)

መቼ ፡ በምድር ፡ ብቻ ፡ አምሮብኝ ፡ የምኖረው
ገና ፡ ኢየሱሴ ፡ መጥቶ ፡ በክብር ፡ እነጠቃለሁ
ነዋሪ ፡ አይደለሁም ፡ አገር ፡ አለኝ ፡ በሠማይ
እኖራለሁኝ ፡ በዚያ ፡ ጭንቀት ፡ ስቃይን ፡ ሳላይ

አዋጅ ፡ ይነገር ፡ አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)
ንጉሥ ፡ ለወደደው ፡ እንዲህ ፡ ተደረገ
ንጉሥ ፡ ለሚወደው ፡ እንዲህ ፡ ተደረገ
እጅግ ፡ በተድላ ፡ ደስታ ፡ ይኸው ፡ አለሁ ፡ በጌታ (፪x)
አዋጅ ፡ ይነገር ፡ አዋጅ ፣ አዋጅ (፪x)

አዋጅ ፣ አዋጅ ፣ አዋጅ ፣ አዋጅ (፮x)