አንተ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (Ante Teleq Neh) - ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር
(Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

Harar Amanuel Menfesawi Maheber 1.png


(1)

እግዚኣብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው
(Egziabhier Tewagi New)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር ፡ አልበሞች
(Albums by Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

አንዴ ፡ አንጎዳጉደህ ፡ ሰማይን ፡ አናውጠሃል
ድንቀኛ ፡ አንጎዳጉደህ ፡ ምድርን ፡ አናውጠሃል
በኃይል ፡ አንጎዳጉደህ ፡ ሁሉን ፡ አናውጠሃል
አቤቱ ፡ እግዚኣብሔር ፡ አንተን ፡ ማን ፡ ይመስላል
በድምፅ ፡ ድንቀኛ ፡ ታንጎዳጉዳለህ
በኃይልህም ፡ ብዛት ፡ ሁሉን ፡ ታደርጋለህ
ግርማህ ፡ የሚያስፈራ ፡ ነው ፡ የሚያስደነግጥ
አሠራርህ ፡ ግሩም ፡ እጅግ ፡ የሚወደድ (፪x)

ሥራህ ፡ ሥራህ ፡ ሥራህ ፡ ትልቅ ፡ ነው
ነፍሴም ፡ እጅግ ፡ ታውቀዋለች
(፪x)
የምድርን ፡ ዳርቻ ፡ በቃልህ ፡ ፈጥረሃል
ለወገግታም ፡ ደግሞ ፡ ሥፍራን ፡ አስታውቀሃል
ለብርሃን ፡ ሁሉ ፡ መኖሪያ ፡ አዘጋጅተህ
ከጨለማም ፡ ደግሞ ፡ ፈጽሞ ፡ ለይተህ
ሁሉን ፡ በጥበብህ ፡ በማስተዋል ፡ ሠራህ (፬x)
አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ሥራህ ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነዉ (፬x)
ሰማያት ፡ የአንተን ፡ ክብር ፡ ይናገራሉ
የሰማይ ፡ ጠፈር ፡ የእጅህን ፡ ሥራ ፡ ያወራል
እንዳንተ ፡ ከቶ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ አል?

እኔም ፡ አላውቅህም ፡ አንተ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፮x)

በሰማየ ፡ ሰማይ ፡ ሰማያቶች ፡ በምድርም ፡ ያሉ ፡ ፍጥረቶች
አዕዋፍ ፡ ሲዘምሩ ፡ ክብርህን ፡ ሲያወሩ ፡ ወንዞች ፡ በፏፏቴ ፡ አንተን ፡ ሲያናግሩ
እኔ ፡ እገረማለሁ ፡ እገረማለሁ
እግዚኣብሔር ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እላለሁ
እኔ ፡ እገረማለሁ ፡ እገረማለሁ
እግዚኣብሔር ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እላለሁ (፪x)