አልፈራም (Alferam) - ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር
(Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

Harar Amanuel Menfesawi Maheber 1.png


(1)

እግዚኣብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው
(Egziabhier Tewagi New)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር ፡ አልበሞች
(Albums by Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

እኔ ፡ የማመልከው ፡ ወረትን ፡ አያውቅም (፪x)
እውነተኛ ፡ ፍቅር ፡ አለው ፡ ለሰው ፡ ልጆች (፬x)

ነፍሴ ፡ ወዳዋለችና ፡ ይሄንን ፡ ጌታ
ሁሌ ፡ ታመልከዋለች ፡ ጠዋትና ፡ ማታ (፪x)

ነፍሴ ፡ እንደዋላ ፡ አንተን ፡ ተጠማች (፪x)
መንፈሴም ፡ በውስጤ ፡ አንተን ፡ አለች
ሥጋዬም ፡ ሁልጊዜ ፡ አንተን ፡ ናፈቀች (፪x)

ኢየሱስ ፡ እርካታ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ እረፍቷ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ሰላሟ ፡ ነህ
ለእርሷ ፡ ፍቅር ፡ ያለህ (፪x)

ሁልጊዜ ፡ አንተን ፡ ትላለች ፡ በፍቅርህም ፡ ተይዛለች
ያለ ፡ አንተ ፡ አይሆንላት ፡ እረዳት ፡ ስለሆንካት (፪x)
እረዳት ፡ ስለሆንካት ፣ እረዳት ፡ ስለሆንካት (፪x)

ከምወድህ ፡ በላይ ፡ ነህ
ከማፈቀርም ፡ በላይ
ከተገመትከው ፡ በላይ ፡ ነህ
ከተባለልህ ፡ በላይ ፡ ነህ (፪x)

ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ኃያል ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ

ብቻህን ፡ ድንቅ ፡ የምትሰራ
ልጆችህን ፡ የምታኮራ
ዘወትር ፡ ነህ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
አንተን ፡ ይዤ ፡ እንደምን ፡ ልፍራ (፬x)

አልፈራም ፡ ብርቱ ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ ፡ አልፈራም
አልፈራም ፡ ኃያል ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ ፡ አልፈራም
አልሰጋም ፡ ብርቱ ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ ፡ አልሰጋም
አልሰጋም ፡ ኃያል ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ ፡ አልሰጋም

አልፈራም ፡ ብርቱ ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ ፡ አልፈራም
አልፈራም ፡ ኃያል ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ ፡ አልፈራም
አልፈራም (፬x)