አዲስ ፡ ምሥጋና (Addis Mesgana) - ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር
(Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

Harar Amanuel Menfesawi Maheber 1.png


(1)

እግዚኣብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው
(Egziabhier Tewagi New)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐረር ፡ አማኑኤል ፡ መንፈሣዊ ፡ ማህበር ፡ አልበሞች
(Albums by Harar Amanuel Menfesawi Maheber)

አንተ ፡ ግን ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ (፬x)
ጊዜ ፡ አይለውጥህ ፡ ቦታ
ሥፍራ ፡ አይወስንህ ፡ ጌታ
ዕድሜ ፡ አይገድብህ ፡ ኢየሱስ
ዘመን ፡ አይሽርህ ፡ ንጉሥ (፪x)

ኢየሱስ ፡ ኃያል ፡ ነህ
በጉልበትህ ፡ አቻ ፡ የሌለህ
ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ
በውበትህ ፡ መሳይ ፡ የሌለህ
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ዘለዓለማዊ
ያልህ ፡ የነበርክ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኗሪ
(፪x)

ኤልሻዳይ ፣ ኤልሻዳይ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ
አዶናይ ፣ አዶናይ ፡ የሌለህ ፡ መሳይ (፪x)

ምን ፡ ብዬ ፡ ላመስግንህ (፪x)
ስንቱን ፡ አውርቼ ፡ እዘልቀዋለሁ
ውለታህ ፣ ውለታህ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x)

ለእግዚአብሔር ፡ አዲስ ፡ ምሥጋና (፫x)
ይብዛ ፡ ይብዛ ፡ ይብዛ ፡ እንደገና
ይብዛ ፡ ይብዛ ፡ ይብዛ ፡ እንደገና (፪x)

ተዓምርን ፡ አድርጐና ፡ ማዳኑን ፡ አስታውቋልና
በአህዛብ ፡ ፊት ፡ ጽድቁን ፡ ገለጠ
ለያዕቆብ ፡ ምህረቱን ፡ ሰጠ
ለእስራኤል ፡ ቤት ፡ እውነቱን ፡ አሰበ
ለእኔም ፡ ደግሞ ፡ ምህረቱን ፡ አበዛ
ለእስራኤል ፡ ቤት ፡ እውነቱን ፡ አሰበ
ለእኔም ፡ ደግሞ ፡ ምህረቱን ፡ አበዛ (፪x)