ለመቅደም (Lemekdem) - ሀፒ ጸጋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀፒ ጸጋዬ
(Happy Tesgaye)

Lyrics.jpg


(Volume)

Single
(Single)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀፒ ጸጋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Happy Tesgaye)

ሲሞላም መዘመር ሲጎልም መዘመር
በዙፋኑ ላለው ከፍ ላለው ለእግዚአብሔር (፪x)

ችግር አላወራም ውድቀት አላወራም
ሽንፈትን ዘምሬ አልገላለጥም
ነገ ድል ይሆናል ጽድቅ ይለመልማል
ልባርከው እየሱሴን እያልኩት ይችላል

ይችላል ይችላል
ይችላል ይችላል
እየሱስ ይችላል (፪x)

እየሱስ
እየሱስ ማንነቴ እየሱስ ጉብዝናዬ
እየሱስ ሙሉነቴ
እየሱስ (፪x)

አዝ፦ ለመቅደም አንተን ማስቀደም ነው
የድልም ሚስጥር ጽድቅህን መፈለግ
ማሸነፍ አንተን ማስቀደም ነው
መንግስትህ ሌላ የሚያስጨምር ነው (፪x)

ስለዚህ ላስቀድምህ ጌታ እግዚአብሔር
ስለዚህ አስቀደምኩህ የኔ እግዚአብሔር (፬x)


ዋናዬ አንተ ነህ አልፈልግም ሌላውን
አይኖቼ ይከፈቱ እንዳስተውል ቃልህን (፪x)

እንደ ቃልህ ስኖር ልክ እንደ ሀሳብህ
እደላደላለሁ እዛ በቤትህ
እንደ ቃልህ ስኖር ልክ እንደ ሀሳብህ
ፈውስ ይሆንልኛል እዛ በቤትህ

እየሱስ
እየሱስ ማንነቴ እየሱስ ጉብዝናዬ
እየሱስ ሙሉነቴ
እየሱስ (፪x)

ስለዚህ ላመስግንህ ጌታ እግዚአብሔር
ስለዚህ ላመስግንህ የኔ እግዚአብሔር
ስለዚህ ከፍ ላደርግህ ጌታ እግዚአብሔር
ስለዚህ ላመስግንህ የኔ እግዚአብሔር

ስለዚህ ላመስግንህ ጌታ እግዚአብሔር
ስለዚህ ልባርክህ የኔ እግዚአብሔር
ስለዚህ ላመስግንህ ጌታ እግዚአብሔር
ስለዚህ ልባርክህ የኔ እግዚአብሔር