From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ሀና ፡ አላዩ (Hannah Alayou)
|
|
፩ (1)
|
NL (NL)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፰ (2016)
|
ቁጥር (Track):
|
፪ (2)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የሀና ፡ አላዩ ፡ አልበሞች (Albums by Hannah Alayou)
|
|
እኔ የተፈጠርኩበት አላማ አንድ ነው
እርሱም አንተን ለማምለክ ነው
እኔ የተሰራሁበት አላማ አንድ ነው
እርሱም አንተን ለማምለክ ነው
ላምልክህ ልውደድህ ልቅረብህ ልጠጋህ
ሳላመልክህ እንዴት እኖራለው
አንተን ላመልክ እኔ ወስኛለው
ከእግሮችህ ስር ዝቅ ዝቅ ልል
ቅዱስና የተፈራህ ልልህ
አምላክ ነህ አምላክ ነህ የማትጠገብ
ንጉስ ነህ ንጉስ ነህ እንከን የሌለህ
ፍቅር ነህ ፍቅር ነህ ጌታ ኢየሱስ
እመጣለው ዙፋንህ ስር
እሰግዳለው ከእግሮች ህ ስር
እቀኛለው አዲስ ቅኔ
ክበርበት መድህኔ
አንተን ማምለክ እወዳለው ላንተ መኖር እሻለዉ
ይሄን ካላረኩኝ ህይወት ትርጉሙ ምንድን ነው
ኑሮስ ጣዕሙ ምንድን ነው
ስለዚህ ሃሳቤን ሰብስቤ ዓይኔን የሱስ ላይ አድርጌ
ላምልክ ላምልክ ሁል ጊዜ
ይሰበር ናርዶሴ ያውድህ መስዕዋቴ
ይሰበር ብልቃጡ ይሽተትህ መስዕዋቱ
ይሰበር ናርዶሴ ይሽተትህ መስዕዋቴ
ይሰበር ብልቃጡ ያውድህ መስዕዋቱ
ተቀበለው እንካ ውሰደው
መልካሙን መዓዛ አንተ አሽትተው
ወዳጄ አሽተተው
ዉድዬ አሽተተው
ያህዌ አሽተተው
ኤሎሄ አሽተተው
ንጉስ አሽተተው
ዝም አትበለው
|