From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ሀና ፡ አላዩ (Hannah Alayou)
|
|
፩ (1)
|
Nigus Lewededew (Nigus Lewededew)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፰ (2016)
|
ቁጥር (Track):
|
፭ (5)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የሀና ፡ አላዩ ፡ አልበሞች (Albums by Hannah Alayou)
|
|
የሚያረካኝ x 3 እኔን የሚያስደስተኝ
ሲከብር ሳየው ኢየሱሴን በህይወቴ ዘመን
ጥንት አባቶቼ እንዳስከበሩት
ፈቃዱን አርገው እንዳንቀላፉት
ፈቃድህ ይሁን በኔም ህይወት
ከፍ ብለህ ታይ ጌታ ኢየሱስ
የሚያረካኝ x 3 እኔን የሚያስደስተኝ
ሲከብር ሳየው ኢየሱሴን በህይወቴ ዘመን
ከክፋት ርቆ ክሃጥያት ሸሽቶ
በቅድስና ካንተ ጋር ኑሮ
በህልውናህ ውስጥ ተጥለቅልቆ
መኖር ልዩ ነው ካንተ ጋር አብሮ
የሚያረካኝ x 3 እኔን የሚያስደስተኝ
ሲከብር ሳየው ኢየሱሴን በህይወቴ ዘመን
ፊቴ ያለውን ሩጫ በትግስት ሮጬ
የዕምነትን ገድልም ተጋድዬ
ያለኝን ሁሉ አፅንቼ ይዤ
አክሊል ልቀበል ድልን ነስቼ
እርካታዬ ጥማቴ ጉጉቴ
ሲከብር ሳየው ነው ኢየሱሴ
ልቆ ሲታይ ነው ኢየሱሴ
|