ምስጋና (Mesgana) - ሀና ፡ አላዩ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ አላዩ
(Hannah Alayou)

Hannah Alayou 1.jpg


(1)

nigus lewededew
(Nigus Lewededew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ አላዩ ፡ አልበሞች
(Albums by Hannah Alayou)

ሰው ነኝና እስቲ ምላሽ ልስጠው
እንደ ግዑዝ ዝም ብዬ አልለፈው
ያረገልኝ ብዙ ድንቅ ስራ
ሰዓት አይበቃም ቢተረክ ቢወራ

ኦ የምስጋናን ንዶ
ኦ የዝማሬ ድምፅ
ኦ ከሆዴ የሚፈልቅ
ኦ ላምላኬ ይሁን

ለኢየሱስ ይሁን
ልውዴ ይሁን
ለንጉስ ይሁን

ላምላኬ ይሁን
ለኢየሱስ ይሁን
ልውዴ ይሁን

ምስጋና በምስጋናው ላይ ምስጋና
ዝማሬ በዝማሬው ላይ ዝማሬ
ላምላኬ እንደሚገባው አውቄ
መጣለው መስዋዕቱ ስፍራ አምልኮዬን ይዤ

ይዤ መጣለው በፊቱ ምስጋና
ይዤ መጣለው አምልኮ

ያዘጋጀው በአፌ ምስጋንና
ቂመኛውን ጠላቴን ሊመታ
ስለዚህም እጅግ ደስ ይለኛል
ጠላት መምቻን መሳሪያ ሰቶኛል

ኦ ምስጋና ሚሰዋ
ኦ ጌታን ያከብረዋል
ኦ ጠላት የሚመታው
ኦ በከበሮ ሆንዋል
በዝማሬ ሆንዋል
በእልልታ ሆንዋል
በምስጋና ሆንዋል

በእልልታ ሆንዋል
በጭብጨባ ሆንዋል
በከበሮ ሆንዋል

ምስጋና በምስጋናው ላይ ምስጋና
ዝማሬ በዝማሬው ላይ ዝማሬ
ላምላኬ እንደሚገባው አውቄ
መጣለው መስዋዕቱ ስፍራ አምልኮዬን ይዤ x

አለኝ ምስጋና አለኝ, አለኝ አምልኮ አለኝ
አለኝ እልልታ አለኝ, አለኝ ጭብጨባ አለኝ
ዙፋኑን ይክበብልኝ, ማደሪይውን ያስጊጥልኝ

ልቤ ጨከነ ልቤ ቆረጠ
ሊያመልክህ ተነሳሳ አንተን አንተን አለ

የገባብኝ ፍቅር ውስጤን የነካኝ
መች ያስቀምጠኛል ይለኛል አመስግኝ
በጠዋት በማታ አንተን አመልካለው
ልዑል ሆይ ለስምህ ክብር ላንተ ዘምራለው

ዝም አልልም አመሰግናለው
ዝም አልልም አሞግሰዋለው
ዝም አልልም አዜምለታለው
ዝም አልልም ተባረክ እላለው