ማምለክ ነው ስራዬ (Mamlek New Sraye) - ሀና ፡ አላዩ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሀና ፡ አላዩ
(Hannah Alayou)

Hannah Alayou 1.jpg


(1)

አልበም
(Nigus Lewededew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ አላዩ ፡ አልበሞች
(Albums by Hannah Alayou)

ማምለክ ፤ ማምለክ :ነው ስራዬ፤
ሌላ ምን ልበልህ ጌታዬ፤
ሰማይና የብሱን ባህሩን ፈጥረሃል
አንተን ማምለክ ብቻ የኔ ስራ ሆንዋል።

ማድነቅ ፤ ማድነቅ ነው ስራዬ፤
ሌላ ምን ልበልህ ጌታዬ፤
ሰማይና የብሱን ባህሩን ፈጥረሃል
አንተን ማምለክ ብቻ የኔ ስራ ሆንዋል።

ስራዬ ነው ጥሪዬ ነው፤
አንተን ማሞገስ ማወዳደሱ፤
ዕድል ፈንታዬ ዕጣ ክፍሌ፤
ኢየሱሴ ነው ለኔ ድርሻዬ።

በጠዋትና በቀን በማታ፤
እንዳሞግስህ ክብርን እንዳመጣ፤
መሰዊያህንም እንዳሳምር፤
ለዚ ታላቅ ክብር እኔን ጠራህ።

የሰማያት መለአክቱ፤
ያለማቋረጥ አንተን ያመልካሉ፤
ቅዱስ ቅዱስ እያሉ፤
ለተረደው በግ ስግደት ያመጣሉ።

እኔም እስግዳለው x3
እኔም አመልካለው
ሁሌም አመልካለው x2

እንዳመልክህ ከተፈጠርኩኝ፤
ደኃዋላ እንዴት እላለሁኝ፤
እንድሰዋ ከተሰራሁኝ፤
መሰዊያህን አሳምራለሁኝ።

አምልኬ አምልኬ አምልኬ አልጠግብ አልኩኝ፤


ዘምሬ ዘምሬ ዘምሬ አልጠግብ አልኩኝ
እንደ እግዚአብሔር ያለ ስላላገኘሁኝ
እንደ ኢየሱስ ያለ ስላላገኘሁኝ

ማምለክ ማምለክ እግዚአብሔርን ማምለክ
እኔም ቤቴም ማምለክ
በጊዜውም ማምለክ
ያለጊዜው ማምለክ
ሲሆን ሳይሆን ማምለክ
ሲጨላልም ማምለክ
ሲነጋጋ ማምለክ