ሁሉ ፡ ከንቱ (Hulu Kentu) - ሀና ፡ አላዩ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ አላዩ
(Hannah Alayou)

Hannah Alayou 1.jpg


(1)

Nigus Lewdedew
(Nigus Lewdedew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ አላዩ ፡ አልበሞች
(Albums by Hannah Alayou)

እንዴት ትልቅ ዕድል ነው እግዚአብሔርን መከተል
ከዛም ደሞ አልፎ ተርፎ እግዚአብሔርን ማገልገል
ሁሉ ከንቱ ዎዎዎ የከንቱ ከንቱ ነው
ሁሉ ጠፊ ሄይ ሃላፊ ነው እግዚአብሔር
ማሰብ ግን እጅግ ጥበብ ነው

ንጉሱ ዳዊት አንተን አገልግሎ
ሄደ አንቀላፋ ሩጫውን ጨርሶ
የኔም መሻት ምኞት ይሄ ነው ጌታዬ
ልሂድ ልከማች ካባቶቼ ጋር አንተን አገልግዬ


እንዴት ትልቅ ዕድል ነው እግዚአብሔርን መከተል
ከዛም ደሞ አልፎ ተርፎ እግዚአብሔርን ማገልገል
ሁሉ ከንቱ ዎዎዎ የከንቱ ከንቱ ነው
ሁሉ ጠፊ ሄይ ሃላፊ ነው እግዚአብሔር
ማሰብ ግን እጅግ ጥበብ ነው

የጭንቅ ቀናቶች ወዳንተ ሳይመጡ
ደስ የማያሰኙም አመታት ሳይደርሱ
ጨረቃና ፀሃይ ከቶ ሳይጨልሙ
ፈጣሪን አስብ ጊዜው ሳያልፍ ይልቅ ከውዲሁ

እንዴት ትልቅ ዕድል ነው እግዚአብሔርን መከተል
ከዛም ደሞ አልፎ ተርፎ እግዚአብሔርን ማገልገል
ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው
ሁሉ ጠፊ ሃላፊ ነው እግዚአብሔር
ማሰብ ግን እጅግ ጥበብ ነው

ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው
ሁሉ ጠፊ ሄይ ሃላፊ ነው እግዚአብሔር
ማሰብ ግን እጅግ ጥበብ ነው

ወንድሜ ሆይ ስማ አንድ ነገር ልንግርህ
እግዚአብሔር ይበልጣል ከሁሉም ነገር

አንተ ወጣት ስማኝ አንድ ነገር ልንግርህ
እግዚአብሔር ይበልጣል ከሁሉም ነገር

እህቴ ሆይ ስሚኝ የህይወት ቃል ልንግርሽ
እግዚአብሔር ይበልጣል ከሁሉም ነገር

ሁሉ ከንቱ ዎዎዎ የከንቱ ከንቱ ነው
ሁሉ ጠፊ ሃላፊ ነው እግዚአብሔር
ማሰብ ግን እጅግ ጥበብ ነው