ሃሌሉያ (Hallelujah) - ሀና ፡ አላዩ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ አላዩ
(Hannah Alayou)

Hannah Alayou 1.jpg


(1)

Nigus Lewededew
(Nigus Lewededew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ አላዩ ፡ አልበሞች
(Albums by Hannah Alayou)

ከፍ ያለነው እግዚያአብሔር
የተፈራ በዙፋኑ ያለና የሚኖር እስከዘላለሙ
ሁሉም ዝቅ ሊልለት ሊሰግድለት ከግሩ ስር የተገባ ነው

ከፍ ያለነው አምላካችን
የተፈራ በዙፋኑ ያለና የሚኖር እስከዘላለሙ
እኔም ዝቅ ልልለት ልሰግድለት ከግሩ ስር የተገባ ነው

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ

እጆቼን አንስቼ ሃሌ ሉያ እይልኩኝ
ሁሌ አንተን ሳመልክህ እኔ ረካለሁኝ
መስዋዕቴ ይኸው ላንተ ይሽተት ህ
ክቡርና ታላቅ አንተን ብቻ ነህ

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ

መላእክቶችህ ሁሉ አንተን ያመልኩሃል
ሌትና ቀን ወድቀው ቅዱስ ነህ ይሉሃል
እኔም ከነርሱ ጋር ይኸው ተባብሬ
አመልክሃለሁኝ ቅዱስ ቅዱስ ብዬ

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ

ከእልፍ የተመረጥክ መልከመልካም አምላክ
ውበትህ ቁንጅናህ ከሰው ልጆች ያምራል
የቆላ አበባዬ የሳሮን ፅጌረዳ
ውዴ ወድሃለው አምልኮዬን እንካ

ሁሉ በሁሉ ነው
ሁሉም ያለው ነው
የሰማይ የምድር
የፍጥረት ገዢ ነው


}}