ከሞት ባሻገር (Kemot Bashager) - ሃና ተክለ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሃና ተክለ
(Hana Tekle)

Lyrics.jpg


(4)

መሥዋዕት
(Meswaet)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፲ ፮ (16)

ርዝመት (Len.): 5:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ተክለ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ተስፋ እንደሌላቸው በምሬት እኛ አናዝንም
በስጋ ከምንወዳቸው መለየት በእርግጥ ቢያምም
የዘላለም ተስፋ አለን ከሞት ወዲያ
በዚያ እንገናኛለን በንጉሥ ማደሪያ
ተስፋ እንደሌላቸው በምሬት እኛ አናዝንም
በስጋ ከምንወዳቸው መለየት በእርግጥ ቢያምም
የዘላለም ተስፋ አለን ከሞት ወዲያ
በዚያ እንገናኛለን በኢየሱስ ማደሪያ

የቅዱሳን ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው
ይህንን ክብር የሚያገኝ ሰው ማነው?
በእርግጥ ቢለይም ከወዳጆቹ ከዚህኛው አለም
ኢየሱስ አለ የተቀበለው ለዘለዓለም
የፃድቁ ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው
ይህንን ክብር የሚያገኝ ሰው ማነው?
ሲሄድ ቢለይም ከወዳጆቹ ከዚህኛው ዓለም
ኢየሱስ አለ የተቀበለው ለዘለዓለም

አለኝ ቤት አለኝ-አለኝ በሰማይ
አለኝ ቤት አለኝ-አለኝ በሰማይ
በእጅ ያለተሰራ-የሰማይ ሀገር
አለኝ መኖሪያ- ከዚህ ስሻገር
አለን ቤት አለን-አለን በሰማይ
አለን ቤት አለን-አለን በሰማይ
በእጅ ያለተሰራ-የሰማይ ሀገር
አለን መኖሪያ- ከሞት ባሻገር