አግዚአብሔር (Egziabeher) - ሃና ተክለ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሃና ተክለ
(Hana Tekle)

Lyrics.jpg


(4)

መሥዋዕት
(Meswaet)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 5:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ተክለ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

በሰማይ በምድር አቻ የለህ
ወሰን ልኬት የለው ግዛትህ
ክብርህ ሰማያትን ሸፍኖ
ላይደረስበት አለ ገኖ
እግዚአብሔር እግዚአብሔር

አንተ ሰማያትን ምድርን ሞልተሀል
አለቅነት ስልጣን አንተን ያመልኩሀል
የለም ካንተ በላይ ደርሶ ሚጠጋጋ
ገናናነት ክብር ሁሌም አንተ ጋ
እግዚአብሔር እግዚአብሔር

ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ አንተ
ሀሳብህም ከቶ አይከለከልም
በምድር ያለው ሁሉ ገንዘብህ ነው
ካንተ የተሰወረ የለም ምንም
እግዚአብሔር እግዚአብሔር

ከዜማ በላይ ነው ክብርህ
ከቃላት በላይ ነው ማንነትህ
እግዚአብሔር አንተ ታላቅ ነህ
አንተን መሣይ የሌለህ
እግዚአብሔር እግዚአብሔር