From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ሃና ተክለ (Hana Tekle)
|
|
፬ (4)
|
መሥዋዕት (Meswaet)
|
ዓ.ም. (Year):
|
2024
|
ቁጥር (Track):
|
፲ ፫ (13)
|
ርዝመት (Len.):
|
6:33
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የሃና ተክለ ፡ አልበሞች (Albums by Hana Tekle)
|
|
ጨለማችንን አበራው ኢየሱስ አበራው
የእግዚአብሔር ልጅ ዕዳችንን ከፈለው
ያታገለን የሞት ቀንበር ተሻረ
በበጉ ደም ሕይወታችን ከበረ
ከቋንቋ ከነገድ
ከሕዝብም ሁሉ ከወገን
ይኸው ዋጀን ለመንግስቱ
አደረገን ካህናቱ
ማኀተሙን ይፈታ ዘንድ ድል የነሣው
መጽሐፉን ሊዘረጋ የተቻለው
ታርዷልና ይገባዋል ብዙ ክብር
የይሁዳ ነገድ አንበሳ የዳዊት ሥር
ከቋንቋ ከነገድ
ከሕዝብም ሁሉ ከወገን
ይኸው ዋጀን ለመንግስቱ
አደረገን ካህናቱ
ደሙ ነው ሰው ያረገን
ስሙ ነው ያዳነን
ክቡር ይሁን ለስሙ
ላዳነን በደሙ
ስሙ ነው ሰው ያረገን
ኢየሱስ ነው ያዳነን
ክቡር ይሁን ለስሙ
ላዳነን በደሙ
ሃሌሉያ ሃሌሉያ ክብር ክብር
ለታረደው በግ ኃይልና ባለጠግነት ክብር
ለታረደው በግ ጥበብ ብርታት በረከት -ይገባዋል
የታረደው በግ ኃይልና ባለጠግነት ክብር
የታረደው በግ ጥበብ ብርታት በረከት -ይገባዋል
ምስጋና ምስጋና ምስጋና ይገባዋል
ክብር ክብር ሊቀበል ይገባዋል
|