From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ሀና ፡ ተክሌ (Hana Tekle)
|
|
፬ (4)
|
አልበም (Meswaet)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፲ ፬ (2024)
|
ቁጥር (Track):
|
፭ (5)
|
ርዝመት (Len.):
|
6:32
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች (Albums by Hana Tekle)
|
|
አስቤ አስቤ አስቤ
ያረገልኝን ከልቤ
አመልክሃለሁ ክብሬ ነህ
የከበርኩብህ ስሜ
አስቤ አስቤ አስቤ
የሆንክልኝን ቆጥሬ
አመልክሃለሁ ሃይሌ ነህ
የከበርኩብህ ክብሬ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ
የለኝም አቅምና ጉልበት
እራሴን የማሳይበት
የለኝም ከእግዚአብሔር ሌላ
አላውቅም ፈረስም ሰረገላ
አንድ ነው የእኔ ጉልበት
ደፍሬ ምሰብክለት
እግዚአብሔር ነው መመኪያዬ
አለኝ የምለው ጌታዬ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ
ከበዛው ፍቅርህ በስተቀር
ምን አለኝ ብልስ ልናገር
አልቻልኩም የለኝምና
ያለኝን ይኸው ምስጋና
ከማዳን ድንቅ ጀምረህ
ያቆምከኝ እንዲህ አክብረህ
ያክብርህ ዘሬ በሙሉ
ያምልኩህ አለህ ይበሉ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ
አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ
ይህ አለኝ ይላል የኖረው
ይህ አለኝ ይላል የሞላው
አለኝ ይላል ዶሴውን መዞ
ይህ አለኝ ይላል ያለውን ቆጥሮ
እኔስ የለኝም ዶሴ
አለኝ የምለው በራሴ
እኔ አሳያለሁ ክብሬን የሞላኝን
እኔ አሳያለሁ ሃብቴን የእግዚአብሔሩን
ጉልበቴ ሆይ አቅሜ ነህ
የኔ እግዚአብሔር ጋሻዬ ነህ
ጉልበቴ ሆይ አቅሜ ሆይ
የኔ እግዚአብሔር ጋሻዬ ሆይ
እንዳንተ የረዳኝ ማነው
እንዳንተ ያከበረኝ ማነው
ለኔ እንዳንተ ማነው
ለኔ እንዳንተ ማነው
ብርታቴ ሆይ ሞገሴ ነህ
የኔ ክብር ማዕረጌ ነህ
ብርታቴ ሆይ ሞገሴ ሆይ
የኔ ክብር ማዕረጌ ሆይ
ለኔ እንዳንተ ማነው
ለኔ እንዳንተ ማነው
ለኔ እንዳንተ ማነው
ለኔ እንዳንተ ማነው
|