ወዳጅ (Wedaj) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Lyrics.jpg


(4)

መሥዋዕት
(Meswat)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2024)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:57
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

3-ወዳጅ

ውስጤ ባንተ አረፈ
ልቤ ባንተ ሰከነ
ወዳጅ የሚባል አገኘሁ
ኢየሱስ ካንተ ተወዳጀሁ
ውስጤ ባንተ አረፈ
ነፍሴ ባንተ ሰከነች
ወዳጅ የሚባል አገኘሁ
ኢየሱስ ባንተ ተረጋጋሁ

ያለሁበት አለህ ከጎኔ
አትጠፋም ከውስጤ ከቤቴ
የልቤ ነህ ሰላሜ
ጓደኛ የዘላለሜ

እንደአይንህ ብሌን ምትሳሳልኝ
ተግተህ የምትወደኝ ምትጠብቀኝ
ኢየሱስ...
የዘላለም ወዳጄ ነህ ኢየሱስ
የቤቴ እረፍት የህይወቴ ንጉስ
የዘላለም ወዳጄ ነህ ኢየሱስ
የቤቴ ራስ የህይወቴ ንጉስ
ወዳጅነትህ አያልቅም
ፍቅርህ በሰሞን አይደርቅም
ወረት በሌለው ፍቅር ይዘኸኛል
ለዘላለሙ ወደኸኛልወዳጅነትህ አያልቅም
ፍቅርህ በዘመን አይበርድም
ወረት በሌለው ፍቅር ይዘኸኛል
ለዘላለሙ ወደኸኛል
የዘላለም ወዳጄ ነህ ኢየሱስ
የቤቴ እረፍት የህይወቴ ንጉስ
የዘላለም ወዳጄ ነህ ኢየሱስ
የቤቴ ራስ የህይወቴ ንጉስ

1,በፍቅርህ ይዘኸኝ አለሁ
ይኸው ዛሬም ባንተ እመካለሁ
የልቤ ወዳጅ እያልኩኝ ዘመኔን እዘምራለሁ
ወገን ነህ ዘመድ ጓደኛ
የብቸኝነት መዳኛ
ያለሁበት አለህ ከጎኔ
አትጠፋም ከውስጤ ከቤቴ
የልቤ ነህ ሰላሜ
ጓደኛ የዘላለሜ
 
2,የማላስረዳህ ነህ ንግግሬን
አላብራራም ላንተ አባባሌን
የልቤ ቀድሞ የሚገባህ
የምትረዳኝ ሳላወራህ
ወዳጄ ነህ ነፃነቴ
ሰርክ የሚገባህ ስሜቴ
ለሚስጥሬ የማላፍርብህ
ለጓዳዬ የማልሰጋብህ
የልቤ ነህ ሰላሜ
ጓደኛ የዘላለሜ

ያለሁበት አለህ ከጎኔ
አትጠፋም ከውስጤ ከቤቴ
የልቤ ነህ ሰላሜ
ጓደኛ የዘላለሜ