ቅዱስ (Kidus) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Lyrics.jpg


(4)

Mesewaet
(Mesewaet)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2024)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:24
ጸሐፊ (Writer): ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ያለህና የነበርህ በክብር የምትመጣ
ለዘላለም የምትኖር የሰማይ የምድር ጌታ
ምድር ከክብርህ ተሞልታለች ያንተን ክብር እያየች
እኛም ባርያዎችህ በፊትህ እንሰግዳለን

ቅዱስ/12
እንዳንተ የለም ጌታ በሃይል የበረታ
እንዳንተ የለም ጌታ በክብር የበረታ

በፅድቅ ነው ክብረ ዙፋንህ
ሁሉን ቻይ ግርማዊነትህ
የገዢዎች ገዢ ነህ ሃያል ሽረት የማይደርስብህ
ሰማይ ሰራዊት ያመልኩሃል
ልዑል ግርማህ ያስፈራል
ትልቁን ሃይል ይዘህ ነግሰህ ማን ችሎ ፊትህ ይቆማል

ቅዱስ/12
እንዳንተ የለም ጌታ በሃይል የበረታ
እንዳንተ የለም ጌታ በክብር የበረታ

በሰማይ በምርድ የለም አንተን የሚመስልህ
የዘመን ቁጥር የለም የሚገድብ
ምድር ከክብርህ ተሞልታለች
ታላቅነትህን ታውጃለች

በሰማይ በምርድ የለም አንተን የሚመስልህ
አልፋና ኦሜጋ ነህ አንተ ለብቻህ
ምድር ከክብርህ ተሞልታለች
አምላክነትህን ታውጃለች

እንዳንተ ያለ የለም በሰማይ
እንዳንተ ያለ የለም ምድር ላይ

ከምድርም በታች የለም
አይኖርም ለዘላለም/2