በማለዳ (Bemaleda) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Lyrics.jpg


(4)

Bemaleda
(Bemaleda)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2024)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:58
ጸሐፊ (Writer): ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

የተገባህ ምስጋና አንተ ነህ የኔ ጌታ
የተገባህ ክብር ላንተ ነው የኔ ጌታ
በምስጋና ወደ ፊትህ እቀርባለው ላመልክህ
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ይገባሃልና ለስምህ

በምስጋና የተፈራህ ገናና አምላክ ነህ
ልዑል አምላክ ብንዘምርህ ብንሰግድልህ አይበቃህም
አእላፋት ያንተ ፍጥረት ላንተ ክብር ያዜማሉ
ቀን ከለሊት ያንተን ስራ በምስጋና ያውጃሉ

በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ እኔ አበዛለሁ
በቀትርም ዝማሬዬን አበዛለሁ አበዛለሁ
በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ እኔ አበዛለሁ
በለሊትም ዝማሬዬን አበዛለሁ አበዛለሁ

ስምህ ሃያል የአማልክቱም አምልካክ ገዢ ነህ
ታላቅ ጌታ የሆነልህ ሰማይ ምድሩ ምስጋናህ
መላእክቱ ላንተ ሞገስ ላንተ ግርማ ይዘምራሉ
ባይገልፅህም ባዲስ ቅኔ ምስጋናህን ያውዳሉ

በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ እኔ አበዛለሁ
በቀትርም ዝማሬዬን አበዛለሁ አበዛለሁ
በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ እኔ አበዛለሁ
በለሊትም ዝማሬዬን አበዛለሁ አበዛለሁ

ለኔ ብዙ ተደርጎልኛል ለኔ ብዙ ሆኖልኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይሻለኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይገልፅልኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይበጀኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይገልፅልኛል

ለኔ ብዙ ሆኖልኛል ለኔ ብዙ ተደርጎልኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይሻለኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይገልፅልኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይበጀኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይገልፅልኛል

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን/2
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን/2
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን/2