From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ሀና ፡ ተክሌ (Hana Tekle)
|
|
፬ (4)
|
Meswat (መሥዋዕት)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፲ ፬ (2024)
|
ቁጥር (Track):
|
፱ (9)
|
ርዝመት (Len.):
|
7:38
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች (Albums by Hana Tekle)
|
|
አልተረሳሁም ባንተ ዘንድ
ከቶ አተወኝም ከመንገድ
የሁልጊዜ ነው ወዳድነትህ
አትለወጥም ሁኔታን አይተህ
አልተረሳሁም ባንተ ዘንድ
ከቶ አተወኝም ከመንገድ
የሁልጊዜ ነው ወዳድነትህ
አትለወጥም ሁኔታን አይተህ
ታውቀኛለህ አንተ በስሜ ከቶ አተወኝም
አትረሳኝም አንተ ሰውን ከቶ አትጥልም
በዚህ እፅናናለሁ አንተን አይሀለሁ
በዚህ እፅናናለሁ እበረታለሁ አንተን ብቻ አይሀለሁ
ኢየሱስ... የልቤ ጌታ ውስጤን አዋቂ
ኢየሱስ... ባገኘኝ ሁሉ ልቤን ጠባቂ
ተስፋዬ አንተ ብቻ ነህ የልቤ ብርታት
የመኖር አቅሜ የልቤ ጠገን የልቤ ፅናት
የለኝም የምመካበት -ልቤን የማስጠጋበት
የውስጤን አንተ ታውቃለህ-ልቤን ትደግፋለህ
የለኝም የምፅናናበት- ልቤን የምጥልበት
የውስጤን አንተ ታያለህ ልቤን ትደግፋለህ
ኢየሱስ... ያልተፈጠሩ ቀኖቼን ያየህ
ኢየሱስ... ያሰፈርካቸው በክብር ፅፈህ
አምናለሁ ለኔም እንዲህ ነህ አትዘነጋኝም
በእጆችህ መዳፍ የቀረፅከኝን አትረሳኝም
ከመዳፍህ ካልጠፋሁ ካወቅከኝ ይበቃኛል
የተረሳሁ ሲመስለኝ መንፈስህ ያፀናኛል
ከአይኖችህ ፊት ውላለሁ እንደብዙ ሆናለሁ
ታውቀኛለህ በስሜ ሁሉን ባንተ እረሳለሁ
እፅናናለሁ ፊትህን ሳይ
እበረታለሁ ፊትህን ሳይ
ቀና እላለሁ ፊትህን ሳይ
እበረታለሁ አይንህን ሳይ
የለኝም የምመካበት -ልቤን የማስጠጋበት
የውስጤን አንተ ታውቃለህ-ልቤን ትደግፋለህ
የለኝም የምፅናናበት- ልቤን የምጥልበት
የውስጤን አንተ ታያለህ ልቤን ትደግፋለህ
|