From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዲስ ፡ ሰማይ ፡ አዲስ ፡ ምድር
የብርሃን ፡ ሀገር ፡ የብርሃን ፡ ቅጥር
ምርአፍ ፡ ተዘግቶ ፡ ምርአፍ ፡ ሲጀመር
አየዋለው ፡ ያኔ ፡ በድል ፡ በክብር
ሲያልፍ ፡ ፊተኛው ፡ ሰማይ
ደግሞ ፡ አንደገና ፡ አዲስ ፡ ሰማይ
ሲያበቃ ፡ ይሄኛው ፡ ምድር
ዘለዓለም ፡ አለ ፡ የክብር ፡ ምድር (፪x)
ጨለማ ፡ ዳግም ፡ በማይሰፍነበት
ፀሐይም ፡ ጨረቃም ፡ በሌሉበት
በጉ ፡ ብርሃን ፡ ነዉ ፡ ያበራል
ሀገር ፡ በክርስቶስ ፡ ይደምቃል
አዝ፦ ሀብተ ፡ ሰማይ ፡ ፅኑ ፡ ተስፋዬ
የዘላለም ፡መኖርያዬ
ሀብተ ፡ ሰማይ ፡ የክብር ፡ ተስፋዬ ፡
ከአየሱስ ፡ ጋር ፡ ለዘላለም ፡ መንገሻዬ
አይን ፡ ያላየው ፡ ጆሮም ፡ ያልሰማው
ጌታ ፡ ለሚወዱት ፡ ያዘጋጀው
ልብሳቸውን ፡ በበጉ ፡ ደም ፡ ላጠቡ
የሰፋውን ፡ መንገድ ፡ ጥለው ፡ ለዘለቁ
አዝ፦ ሀብተ ፡ ሰማይ ፡ ፅኑ ፡ ተስፋዬ
የዘላለም ፡መኖርያዬ
ሀብተ ፡ ሰማይ ፡ የክብር ፡ ተስፋዬ ፡
ከአየሱስ ፡ ጋር ፡ ለዘላለም ፡ መንገሻዬ
በተስፋ ፡ ድንበር ፡ በፍቅር ፡ ሀገር
የእምነት ፡ ፅናት ፡ ምላሽ ፡ ሲሰምር
ሲበሰር ፡ የዘለዓለሙ ፡ ደስታ
የታመኑት ፡ የናፈቁት ፡ ላይም ፡ ሲበቃ
አዝ፦ ሀብተ ፡ ሰማይ ፡ ፅኑ ፡ ተስፋዬ
ከአየሱስ ፡ ጋር ፡ ለዘላለም ፡ መኖርያዬ
ሀብተ ፡ ሰማይ ፡ ፅኑ ፡ ተስፋዬ ፡
ከአየሱስ ፡ ጋር ፡ ለዘላለም ፡ መንገሻዬ
ሌት ፡ በማያውቀው ፡ የቀን ፡ ጅረት
ብርሃን ፡ ውሎ ፡ ብርሃን ፡ ማደር
ምናለ ፡ ደስታ ፡ ምናለ ፡ ውበት
ከክርስቶስ ፡ ጋር ፡ ነግሶ ፡ አንደማየት
ሞት ፡ በማይገጥመው ፡ የህይወት ፡ ጅረት
ድል ፡ ከነሱት ፡ ጋር ፡ ተካፍሎ ፡ እርስት
ምናለ ፡ ውበት ፡ ምናለ ፡ ፍሰሃ
አንደመገኘት ፡ ከዚህ ፡ ክብር ፡ ጋር
ሲያልፍ ፡ ፊተኛው ፡ ሰማይ
ደግሞ ፡ አንደገና ፡ አዲስ ፡ ሰማይ
ሲያበቃ ፡ ይሄኛው ፡ ምድር
ዘላለም ፡ አለ ፡ የክብር ፡ ምድር
|