Hana Tekle/Habte Semay/Yetadelen

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በአንተ የተጠራ ወገን በአንተ የተወደደ ከጥፋት ባህር ንዳድ በስምህ የተጋረደ ክብሩ ኢየሱስ የሆንክለት መጠሪያ የዘውድ ስሙ በኪዳንህ የሚራመድ በደምህ የገባህ ከደሙ በክብርህ እሳት የሚነድ በህልውናህ ዓለም በእረፍት ጠል የረሰረሰ ከህዝብህ በቀር የለም የለም ከእኛ በቀር የለም የለም ከህዝብህ በቀር የለም

የታደልን ህዝብ በአንተ ታየን ተመረጥን ተወደድን መስዋዕት በሆንክ በተነሳህ ከሞት ከሞት አመለጥን

ክብራችን ነህ ሞገሳችን ብንዘምርልህ ብንዘምር የማይደክመን ለሰማዩም ለምድሩም መጠጊያ የታመንብህ ጽኑ መጠለያ

ክብራችን ነህ ሞገሳችን ብንዘምርልህ ብንተርክህ የማይደክመን ለሰማዩም ለምድሩም መጠጊያ የታመንብህ ጽኑ መጠለያ

እናመልክሃለን (×፭)


በማይጠፋ ሕይወት በማይሞት ገርስሰህ የዘላለምን ሞት በብርሃንህ ብርሃን አሳየኸን አንተው ባለህበት አሰፈርከን ምን እንላለን? የሱስ ምን አለን?

ክበር ክበር ክበር ክበር ክበር ክበር ክበር ክበር ክበር ክበር እንላለን ንገስ ንገስ ንገስ ንገስ እንላለን

ተሞኝተን አይደለም ምናመልክህ ኢየሱስ ኢየሱስ የምንልህ በደንብ ገብቶናል አንድ ፍቅርህ ልንርቅ እኛ አንችልም ከእቅፍህ

ተሞኝቼ አይደለም የማመልክህ ኢየሱስ ኢየሱስ ሁሌ ምልህ ኧረ እኔስ ገብቶኛል አንድ ፍቅርህ ልርቅ እኔ አልችልም ከእቅፍህ

ምን አለን ከአንተ ውጪ እኛ ምን አለን ከአንተ ውጪ

ምንጠራው አንተን ነው ምንጠራው ምናሳየው አንተን ነው ምናሳየው (x2)