ተናገር (Tenager) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 3.jpg


(3)

ሀብተ ፡ ሰማይ
(Habte Semay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

፲ ፭ (15)

ርዝመት (Len.): 6:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ባነበብን ፡ ቁጥር ፡ ባወቅነው ፡ የማንለምደው ፡ ቃልህን
በገባን ፡ ቁጥር ፡ ባወቅነው ፡ ምንፈልገው ፡ ቃልህን ፡ ነው
ዛሬም ፡ እንድትልልን ፡ ሳይሆን ፡ ልትል ፡ ያሰብከው ፡ ያግኘን
ያለመከልከል ፡ ተናግረህ ፡ ያለገደብ ፡ ስራብን
መንፈስህ ፡ ይግዛን ፡ ይስፈንብን ፡ በሙላት
የልብህ ፡ ሀሳብ ፡ ያጥምደን ፡ የሚያቆመን ፡ ያ ፡ ነው ፡ በጽናት

እናድጋለን ፡ እንጂ ፡ ሰርክ ፡ ወዳንተ
ልናድግ ፡ አይቻለንም ፡ ባንተ ፡ ላይ
ከፍለን ፡ ባወቅንህ ፡ ቁጥር
ዝቅ ፡ እንበል ፡ እንይ ፡ ወደላይ

ምን ፡ ብናውቅ ፡ ጥበብ ፡ ቢጠጋን
ሲመስለን ፡ ያወቅን ፡ የበቃን
አናውቅም ፡ ባወቅን ፡ ቁጥር
ደቀ ፡ መዝሙር ፡ ነን ፡ ሁሌ ፡ ባንተ ፡ ስር

ተማሪዎች ፡ ነን ፡ ሁሌ ፡ ልጆችህ
መቼም ፡ በማንጨርሰው ፡ ትምህርትህ
ከፍለን ፡ ባወቅን ፡ ጥቂት
ትሁት ፡ አድርገን ፡ ባንተ ፡ ፊት

ታማኝ ፡ አድርገን ፡ ለቃልህ
አቅናን ፡ ለውድ ፡ ሀሳብህ
መስታወት ፡ በሆነው ፡ ቃልህ
አብቃን ፡ ለልብ ፡ መንገድህ

ተናገር ፡ ኢየሱስ
ተናገር ፡ በሀይል ፡ እንሰማሀለን
ተናገር ፡ መንፈስቅዱስ
ተናገር ፡ በሙላት ፡ እንሰማሀለን
ተናገር ፡ እንሰማሀለን