ሽኩር (Shekur) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 3.jpg


(3)

ሀብተ ፡ ሰማይ
(Habte Semay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

፲ ፮ (16)

ርዝመት (Len.): 4:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

በእንባ ፡ እንዳልዘራሁ
በለቅሶ ፡ እንዳልወጣሁ
በሃዘን ፡ እንዳላለፍኩ
ነዶዬን ፡ ይዤ ፡ ተመለስኩ
መልካምነትህን ፡ አየው
ጻድቅነትህን ፡ አየሁ
በእንባ ፡ እንዳልነበርኩ
ነዶዬን ፡ ይዤ ፡ ተመለስኩ

ይኸው ፡ ምስጋናዬን ፡ እንካ
ይኸው ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ
ይኸው ፡ ዝማሬዬን ፡ እንካ
ይኸው ፡ እልልታዬን ፡ እንካ

ባንተ ፡ አይደለም ፡ ወይ (፰x)

ስደክም ፡ ያኔ ፡ ዝዬ
ስበረታም ፡ ደግሞ ፡ ደግሜ
ቁልቁለት ፡ ዳገቱ ፡ ሲያዝለኝ
ሽቅብ ፡ መውጣቱ ፡ ሲከብደኝ
የማያልፍ ፡ ሚመስልን ፡ ያን ፡ ዳገት
አልፌው ፡ ስገኝ ፡ ድንገት
አልረሳም ፡ ያን ፡ ቀውጢ ፡ ጊዜ
ሲርቀኝ ፡ ሃዘን ፡ ትካዜ

ይኸው ፡ ምስጋናዬን ፡ እንካ
ይኸው ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ
ይኸው ፡ ዝማሬዬን ፡ እንካ
ይኸው ፡ እልልታዬን ፡ እንካ

ባንተ ፡ አይደለም ፡ ወይ (፰x)

ማን ፡ አለው ፡ ብሎኛል ፡ ስደክም
የተማመንኩበት ፡ ሲከስም
የያዘኝ ፡ ጸጋህ ፡ በብርቱ
በማልፍበት ፡ አልፎ ፡ የረዳኝ ፡ በሌቱ
የብቸኝነቴ ፡ አምላክ
የጓዳዬ ፡ የሚስጥሬ ፡ ጌታ
ሰማህ ፡ ጩኸቴን ፡ ሰማህ
ሰማህ ፡ እንባዬን ፡ ሰማህ

ይኸው ፡ ምስጋናዬን ፡ እንካ
ይኸው ፡ አምልኮዬን ፡ እንካ
ይኸው ፡ ዝማሬዬን ፡ እንካ
ይኸው ፡ እልልታዬን ፡ እንካ

ባንተ ፡ አይደለም ፡ ወይ (፰x)

ሽኩር ፡ ጉዌታ ፡ ሽኩር - ሽኩር (፪x)