ሩጫው (Ruchaw) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 3.jpg


(3)

አልበም
(Habte Semay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ሩጫው ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ሰላምን ፡ ፍለጋ
እርካታን ፡ ፍለጋ
ሁሉም ፡ በየፊናው ፡ ሚለው ፡ ደፋቀና
ሚለው ፡ ጎንበስ ፡ ቀና
ገንዘብ ፡ ቁስን ፡ እንጂ ፡ እረፍት ፡ መች ፡ ይገዛል
በየደረሰበት ፡ ሰው ፡ ሃሳብ ፡ ይገዛል
ጭንቀት ፡ ይሸምታል

እረፍት ፡ መገኛው ፡ ኢየሱስ
ሰላም ፡ ማደሪያው ፡ ኢየሱስ
ደስታ ፡ ሀገሩ ፡ ኢየሱስ
እረፍት ፡ መኖሪያው ፡ ኢየሱስ

ሀብት ፡ ጥሪት ፡ ይዞ ፡ የተትረፈረፈ
ከእድሜ ፡ ልክ ፡ ያለፈ
ሰላም ፡ ከሌለበት ፡ ሰላምን ፡ ፍለጋ ፡ ስንቱ ፡ ነው ፡ የዋለ
የተንከራተተ
ዛሬን ፡ እረፍት ፡ አጥቶ ፡ ለነገ ፡ ያልማል
ነገም ፡ ነገን ፡ ሲቀርጽ ፡ ሳያልቅ ፡ ዘመን ፡ ያልቃል
እረፍት ፡ መገኛው ፡ ኢየሱስ
ሰላም ፡ ማደሪያው ፡ ኢየሱስ
ደስታ ፡ ሀገሩ ፡ ኢየሱስ
እርካታው ፡ መኖሪያው ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ

በላው ፡ ጠጣው ፡ ትርፌ ፡ ምንድነው?
አጌጥኩ ፡ ለበስኩ ፡ ትርፌ ፡ ምንድነው?
ተማርኩ ፡ አወኩ ፡ ትርፌ ፡ ምንድነው?
ምድር ፡ ሞላልኝ ፡ ትርፌ ፡ ምንድነው?

ኸረ ፡ እኔ ፡ በእንጀራ ፡ ብቻ ፡ ኸረ ፡ አልኖርም
ኸረ ፡ እኔ ፡ በምድሩ ፡ ብቻ ፡ ኸረ ፡ አልኖርም
ክፍተቴ ፡ ሌላ ፡ ነው ፡ ጉድለቴ
የማልሞላው ፡ በማንነቴ
እሮጬ ፡ እሮጬ ፡ ትርፌ ፡ የእኔ ፡ ድካም ፡ ነው
የነፍስ ፡ እርካታዬ ፡ ጌታ ፡ በአንተኮ ፡ ነው
እንኳን ፡ ያንተ ፡ ሆንኩኝ ፡ አወኩህ ፡ እንኳን
እንዳልችል ፡ ሆኛለሁ ፡ ለሌላ ፡ እንዳልሆን
የማምነው ፡ እውነት ፡ በፍቅር ፡ ይዞኛል
ሌላ ፡ ሌላ ፡ እንዳላይ ፡ ውስጤን ፡ ሞልተኸዋል

አሰብኩት ፡ እራሴን ፡ ከአንተ ፡ ውጪ
አሰብኩት ፡ ወጥቼም ፡ ከቤትህ
ባዶ ፡ ነኝ ፡ ቅብዝብዝ ፡ የሌለኝ ፡ እረፍት
እኔ ፡ አልችልም ፡ ሰው ፡ አልሆንም ፡ በሌለህበት