ረግቻለው (Regechalew) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 3.jpg


(3)

አልበም
(habte semay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ለሰላሜ ሚሆነኝን አውቂያለሁ አግኝቻለሁ
ለእፎይታዬ ሚበጀኝን አምኛለሁ ተቀብያለሁ
የእግዚአብሄር ልጅ በርቶልኛል በመንፈሱ ረግቻለሁ
ላልወሰድ በምድር ተረት ለዘላለም ታትሜያለሁ

ከአለም ዋኖች በተሰወረ
ከጠቢባን ዘንድ ባልነበረ
የሞኝነት በሚመስል ታምር
አርፍያለሁ ባንተ ማመን ሚስጥር

የማይነጥፍ ነው ሰላሜ የማያርፍ ነው እረፍቴ
ማደርያህ ልሆንህ ፈቅደህ ገብተሃልና ከህይወቴ
የማይደበዝዝ ፍቅርህ ነው ሽንገላም ወረትምበሌለው
ካንተ ያልተቀበልኩት ምን አለኝ ቀረ ምለው??

ባንተ ደስ ብሎኛል ጸጋህ በዝቶልኛል
ረክቻለሁ አመሰግናለሁ
ሰላም ረግቶልኛል ፍቅር ዘልቆልኛል
ረግቻለሁ እባርክሃለሁ

በሰማያዊው በረከት በራስህ ተባርክያለሁ
እዚህ እንዳልናወጥ ከእቅፍህ ገብቻለሁ
አልሸበርም በአለም በሚሰማው ክፉ ወሬ
ባለኸኝ ረግቼ አለሁ በያዝከኝ እስከዛሬ

አንተን ሰጥተኸኛል አንተን ሞልተኸኛል
ረክቻለሁ አመሰግናለሁ
አንተ ሞልተኽኛል
ህይወት በዝቶልኛል
ተባርክያለሁ
ልጅህ ተብያለሁ

አንተን ይዞ ያልረካ ማነው
አንተን ይዞ ያልሰከነ ማነው
አንተን ይዞ የባከነ ማነው
አንተን ይዞ የባዘነ ማነው
እኔ ረክቻለሁ
ሰላም አግኝቻለሁ
ረግቻለሁ አመሰግናለሁ

ለበዛልኝ ሰላም ለበዛልኝ ፍቅርህ
ለበዛልኝ ህይወት ለበዛ ምህረትህ
ይብዛልህ ክብር ይብዛልህ ሞገስ
ይብዛልህ ክብር እየሱስ ይብዛልህ ሞገስ
ይብዛልህ ምስጋና ይብዛልህ ክብር