ካህን (Kahen) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 3.jpg


(3)

ሀብተ ፡ ሰማይ
(Habte Semay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ካህን ፡ በገዛ ፡ ደምህ ፡ አዳንከኝ
ካህን ፡ በገዛ ፡ ቁስልህ ፡ አተረፍከኝ
ከፍለክ ፡ አቆደስከኝ ፡ ህወትህን
ቆርሰ ፡ አካፈልከኝ ፡ ነብስህን
ከዚህ ፡ የጨመረ ፡ ምን ፡ ፍቅር ፡ ይኖራል
ከዚህ ፡ ደርዝ ፡ ያለፈ ፡ ምን ፡ መውደድ ፡ ይገኛል
መስዋት ፡ ከመሆን ፡ ከመሞት ፡ የባሰ
ለነግስ ፡ ነፍስ ፡ ከማጣት ፡ ከማለፍ ፡ ያለፈ
ብልህ ፡ የመውደድ ፡ ጥልቅ ፡ የፍቅር ፡ ዳርቻ
ሕይወቴ ፡ ተገኝቶ ፡ በአንተ ፡ ፍቅር ፡ ብቻ ፡ በክርስቶስ ፡ ብቻ
ሕይወቴ ፡ ተገኝቶ ፡ በአንተ ፡ ፍቅር ፡ ብቻ
ጨለማዩ ፡ በርቶ ፡ በአንተ ፡ ፍቅር ፡ ብቻ (፪x)

በቃል ፡ ብቻ ፡ በአንደበትህ ፡ ፡ መቼ ፡ ወደድከኝ
በግብር ፡ እንጂ ፡ ፡ በእውነት ፡ ትርጉም ፡ ያፈቀርከኝ
ፍቅርን ፡ አሳየኸኝ ፡ ራስህን ፡ ለቀህ
ሆነህ ፡ ከነብስ ፡ ውጭ ፡ በፈቃድ ፡ ተገለህ
ቅን ፡ ደጉ ፡ ታመነ ፡ የዋህ ፡ ስቃይህ ፡ ገባው
ፍቅር ፡ ተገደልህ ፡ ህይወቴ ፡ እንዲገባ
ብልህ ፡ የመውደድ ፡ ጥግ ፡ የፍቅር ፡ ዳርቻ
ሕይወቴ ፡ ተገኝቶ ፡ በአንተ ፡ ፍቅር ፡ ብቻ ፡ በክርስቶስ ፡ ብቻ
ሕይወቴ ፡ ተርፎልኝ ፡ በአንተ ፡ ፍቅር ፡ ብቻ
ጨለማዩ ፡ በርቶ ፡ በአንተ ፡ ፍቅር ፡ ብቻ
ብልህ ፡ የመውደድ ፡ ጥግ ፡ የፍቅር ፡ ዳርቻ
ሕይወቴ ፡ ተገኝቶ ፡ በአንተ ፡ ፍቅር ፡ ብቻ (፪x)

ልታድነኝ ፡ ልታተርፈኝ ፡ ወደህ ፡ የሄድክበት
የሞትህ ፡ ነው ፡ ያልተገባ ፡ በደም ፡ ያለፍክበት
ከሞት ፡ የስቃይ ፡ በእንጨት ፡ ተንጠልጥለህ
ፃዲቅ ፡ ያለሐጢያትህ ፡ ከአባይ ፡ መሐል ፡ ሆነህ
ቅን ፡ ደጉ ፡ ታመነ ፡ የዋህ ፡ ስቃይህ ፡ ገባው
ፍቅር ፡ ተገደልህ ፡ ህይወቴ ፡ እንዲገባ
ብልህ ፡ የመውደድ ፡ ጥግ ፡ የፍቅር ፡ ዳርቻ
ሕይወቴ ፡ ተገኝቶ ፡ በአንተ ፡ ስቃይ ፡ ብቻ ፡ በህመምክ ፡ ብቻ
ብልህ ፡ የመውደድ ፡ ጥግ ፡ የፍቅር ፡ ዳርቻ
ሕይወቴ ፡ ተገኝቶ ፡ በአንተ ፡ ፍቅር ፡ ብቻ

ምልክ ፡ አገልፅህም ፡ ዘመኔም ፡ ያንስሀል
ለፈሰሰው ፡ ደምህ ፡ ምኔስ ፡ ይክስሀል
እንዲያው ፡ ዝም ፡ ብዩ ፡ ቤዛዩ ፡ እልሀለው
በቀረልኝ ፡ እድሜዩ ፡ ሳመልክህ ፡ እኖራለው ፡ አዜምልሀለው
ቤዛዩ ፡ እልሀለሁ (፪x)
ብዙ ፡ በአንተ ፡ ያገኘሁ
አዳኜ ፡ እልሀለሁ (፪x)
ግምት ፡ በአንተ ፡ ያገኘሁ