ሁሉን ፡ በስርህ (Hulun Besereh) - ሀና ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሀና ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 3.jpg


(3)

ሀብተ ፡ ሰማይ
(Habte Semay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:10
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ፊደል ፡ ተግጣጥሞ ፡ የቱ ፡ ቃል ፡ ገለጠህ
ቃላት ፡ ተሰካክተው ፡ ምን ፡ ቢባል ፡ ተረከህ
ያንተን ፡ ልክ ፡ አዋቂ ፡ አንተ ፡ እግዚዓብሔር ፡ ብቻ
እራስህ ፡ ንገረኝ ፡ ምን ፡ እንድልህ ፡ ብቻ

የተባልከው ፡ ሁሉ ፡ ካንተ ፡ በታች ፡ ሆኗል
ለፍጥረት ፡ ሚበዛው ፡ ላንተ ፡ አቅም ፡ አንሶታል
ያንተን ፡ ልክ ፡ አዋቂ ፡ አንተ ፡ እግዚዓብሔር ፡ ብቻ
እራስህ ፡ ንገረኝ ፡ ምን ፡ እንድልህ ፡ ብቻ

መጀመርያም ፡ መጨረሻም ፡ የሌለህ
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ፊተኛም ፡ ኋለኛም ፡ የሌለህ
እግዚዓብሔር ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
የእኔ ፡ ትልቅ ፡ አንተ ፡ ነህ
የእኔ ፡ ጀግና ፡ አንተ ፡ ነህ

ሁሉን ፡ በስርህ ፡ አስተዳዳሪ ፡
በላይ ፡ ለሁሉ ፡ ሁሉን ፡ ፈጣሪ
የግዙፍ ፡ ግዙፍ ፡ የትልቅ ፡ ትልቅ
ቃል ፡ በማይደፍረው ፡ የከፍታ ፡ ጥግ

አንተ ፡ እግዚዓብሔር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ትልቅ ፡ መሳዩን ፡ ትንሽ ፡ ያደረግህ
ጀግና ፡ መሳዩን ፡ ያንበረከክህ
ጠቢብ ፡ መሳዩን ፡ ሞኝ ፡ ያደረግህ
ያለው ፡ መሳዩን ፡ ባዶ ፡ ያደረግህ

የለም ፡ ያሉህ ፡ የሉም
ዛሬም ፡ የሚሉህ ፡ ነገ ፡ አይኖሩም (፪x)
ይገርመኛል ፡ ትጋታቸው ፡ የከንቱነት ፡ ጥበባቸው
ከአንተ ፡ ውጪ ፡ ሕይወት ፡ ማሰባቸው

አንተው ፡ ባበጀኸው ፡ አእምሮ
ባንተ ፡ ጥበብ ፡ ተቀምሮ
እስትንፋስ ፡ ለግሰህ ፡ በእፍታህ
ባምሳልህ ፡ ሰርተኸው ፡ ስታበቃ
የለህም ፡ የሚልህ ፡ ማን ፡ ነው
እኮ ፡ የለህም ፡ የሚልህ ፡ ማን ፡ ነው

ለመኖርህ ፡ የእርሱም ፡ መኖር ፡ ምስክር ፡ ነው (፫x)
ለመኖርህ ፡ የእኔም ፡ መኖር ፡ ምስክር ፡ ነው

ሉዓላዊነት ፡ ከጥንት ፡ ከዓለማት ፡ በፊት ፡ የነበረ
አለህ ፡ የለህም ፡ ቢባል ፡ ከመኖር ፡ ያልተገደበ
እግዚዓብሔር ፡ አለህ ፡ በማደርያህ
እግዚዓብሔር ፡ አለህ ፡ በዙፋንህ
አለህ ፡ በማደርያህ
አለህ ፡ በዙፋንህ