ግታው ፡ ሰበቤን (Getaw Sebebien) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 3.jpg


(3)

ሀብተ ፡ ሰማይ
(Habte Semay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 4:48
ጸሐፊ (Writer): በረከት ተረፈ
(Bereket Terefe
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ከነገር ጅማሬ ፍጻሜ ይልቃል
ቀን ሳለ ጎበዝ ከየት እንደወደቀ ያስባል።
የጅማሬው ውበት የዳነበቱ
ደብዝዞ ሳያልቅ በመንገድ ከንቱ።
በጸጋ ሽፋን ፋኖ ተማምኖ
ስቆ ለውሃ ብዙ አለና የቀረ ባክኖ።

አልፈልገውም ለብታዬን እግሮቼን አድስ
እኔ አልሻም መባከን በልማድ መደንዘዝ።
ግታው ሰበቤን ያደከመኝን
ሰበብ በኩሬን የሚያስንቀኝን፤
ግታው ምክኒያቴን የተጫነኝን
ምክኒያት በኩሬን የሚያስጥለኝን፡፡

መሀል ሰፋሪ እዚም እዚያም
ሁሉ አይቅርብኝ አገም ጠቀም።
የለብታ ወንዝ ከባድ ፈተና
ወይ ያልበረደው ወይ እሳት ያልገባው ገና።
አቋም በሌለው ከከልካይ ማዶ
በነጻ ክልል ይነጉዳል ፈቅዶ።
ግታው ሰበቤን ያለዘበኝን
አክብጄ እንዳልይዝ ያጠመደኝን፤
ግታው ምክኒያቴን የታገለኝን
ለሁለት ጌቶች ያሰለፈኝን።

ነግቶለት ህይወት ጉዞ ጀምሮ
ባንተው ምህረት በስንት ተምሮ።
ከመንከራተት ተርፎ ያልተረፈ
ዛሬም የሚባክን ልቡ ያላረፈ።
       ገና
ዳግም ባርነት ዳግም እስራት
ባልሰከነች ነፍስ ልጓም በሌላት።
ይብቃኝ ምክኒያቴ የተጫነኝ
አጥብቄ እንዳልይዝ ያታገለኝ።
ግታው ምክኒያቴን ያደከመኝን
ትጥቄን ያላላ ያለዘበኝን።

በመንፈስህ አንቃኝ አዚሜን ገፈህ
የታገትኩበትን ገመዴን ፈተህ።
ግታው ሰበቤን ያበረደኝን
ለሁለት ጌቶች ያሰለፈኝን።