From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ሊያገለግልህ ፡ የጠራኸው ፡ በህዝብህ ፡ ፊት ፡ የሾምከው
ስንቱ ፡ ርቆህ ፡ ያገለግላል ፡ ለዝናው ፡ ክብሩ ፡ አድሮ ፡ ይዉላል
ስንቱ ፡ ርቆህ ፡ የራሱን ፡ ክብር ፡ ያገለግላል
ለዝናው ፡ ስሙ ፡ ታግሎ ፡ ይኖራል ፡
ያላንተ ፡ ጉዞ ፡ ስም ፡ ዝናን ፡ ብቻ ፡ ይዞ
የስጋ ፡ ጥረት ፡ በሌለህበት
ያላንተ ፡ ክብር ፡ በእኔነት ፡ ፍቅር
በፀጋ ፡ ካባ ፡ ለራስ ፡ ወከባ
ለከንቱ ፡ መንገድ ፡ ባንተ ፡ ሲነገድ
ፍለጋ ፡ ክብርን
ፍለጋ ፡ ዝናን
ፍለጋ ፡ ብልጫን ፡ ፍለጋ
ፍለጋ ፡ ንዋይን
ፍለጋ ፡ ትኩረትን
ፍለጋ ፡ ፍለጋ
አምልኮተ ፡ ዝና ፡ አምልኮተ ፡ እኔ
በአምልኮ ፡ መልክ ፡ ሽፋን ፡ በፍቅሬ ፡ ተይዤ
በንጉስ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ህዝብ ፡ ላይ
በውድድር ፡ መንፈስ ፡ ምስባክ ፡ ለታይታ ፡
በትወና ፡ ህይወት ፡ የኔን ፡ ለኔ ፡ ዋይታ
ፍለጋ ፡ ክብርን
ፍለጋ ፡ ዝናን
ፍለጋ ፡ ብልጫን ፡ ፍለጋ
ፍለጋ ፡ ንዋይን
ፍለጋ ፡ ትኩረትን ፡ ፍለጋ ፡ ፍለጋ
በሌለህበት ፡ ሳውልህ ፡ ለዝና ፡ ስሜ ፡ ስፈልግህ
ተላላ ፡ የልቤን ፡ ባያገኘው ፡ ካንተ ፡ ማን ፡ ሊሰውረው
ከባዶ ፡ ጩኸት ፡ ከሌለህበት ፡ ዝምታዬ ፡ ካገነነህ ፡
ባለህበት ፡ ክብሬ ፡ ያ ፡ ነው ፡ ያከበረህ ፡ እኔነቴን ፡ የሰበረ
ፍለጋዬ ፡ ይሁን ፡ ለጉዳይህ
ፍለጋዬ ፡ ይሁን ፡ ለሀሳብህ
ፍለጋዬ ፡ ፍለጋዬ ፡ ፡ ይሁን ፡ ለክብርህ
ስራዬን ፡ ትመዝናለህ ፡ ከመንበርህ ፡ ታዬኛለህ
ፍለጋዬን ፡ አጥራው ፡ መንገዴን ፡ ላረካ ፡ የቆምኩለትን ፡ የራስ ፡ ጥሜን
መከሩ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ስራ ፡ አለ ፡ በቤቱ
ወደሞት ፡ ሚነዳ ፡ አለ ፡ በየዕለቱ
በራስ ፡ ፍቅር ፡ ታምሜ ፡ መሽቶብኝ ፡ ይነጋል
ኢየሱስን ፡ ሳያይ ፡ ስንቱን ፡ ሞት ፡ ይቀድማል
እድሜያችን ፡ ቢበዛ ፡ ሰባ ፡ ነው ፡ ቢያልፍ ፡ እንኳን ፡ ሰማኒያ
ምን ፡ አለን ፡ ክብር ፡ ምን ፡ አለን ፡ ንዋይ
ኢየሱስ ፡ ካንተ ፡ ወዲያ
ምን ፡ አለን ፡ ዝና ፡ ምን ፡ አለን ፡ ክብር ፡ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ወዲያ
|