እውነትና ፡ እውነት (Ewnetena Ewnet) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 3.jpg


(3)

አልበም
(3)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

በሰው ክፋት ማዕበል ምድር ስትናወጥ
ፈጣሪ እንኳ በሰራው ፍጡር እስኪፀፀት
የአንድ ኖህ ጎዳና አካሄድ ቢቀና
የሰው ሕይወት አልቀጠለም ወይ እንደገና X2

በውሸት ከተማ እውነት እንግዳ ነው
መስሎ ፀጉረ ልውጥ የሚያውቀው የሌለው
እውነትን በተቀማ ትውልድ
ማን ይሆን የእውነት ዘመድ
ሁሉ ገሸሽ ሲል ለመስቀል ሲደራ
ማን አብሮ ይዘልቃል ከባይተዋር ጋራ

እንደ ውሃና ዘይት አይደሉም ወይ እውነት እና ሃሰት
ምን አንዱ ቢበዛ መቼም አያብሩ ዘላለም በርቀት
በጊዜ ፈተና ወደቅህ ሚለው የለም
በእሳት ንዳድ አልፎ አመድ አያውቀውም
በልዩነት መንገድ በሰላም ይተማል
አጃቢ ሳያሻው ዘላለም ይኖራል X2

የዝምታው ድምፀት ከመብረቅ ጽኑ ነው
አለት ከሚያነቃ ከሚሰነጥቀው
እርሱ ተረጋግቶ አገር ይረበሻል
የለህም የሚለው እንቅልፍ አጥቶ ያድራል
ከብዙ ግርግር አባይ ከዋለበት
እውነት ከሚመስል አሳች ከበዛበት
ዘንድሮም ጉዳዩ ከእውነት ጋር ብቻ
እውነት እና እውነት ከራሱ ጋር ብቻ

በውሸት ከተማ እውነት እንግዳ ነው
መስሎ ፀጉረ ልውጥ የሚያውቀው የሌለው
እውነትን በተቀማ ትውልድ
ማን ይሆን የእውነት ዘመድ
ሁሉ ገሸሽ ሲል ለመስቀል ሲደራ
ማን አብሮ ይዘልቃል ከባይተዋር ጋራ

የታመነ ጓዳው ዮሴፍ ትንሹ ዛፍ
ባልዋለበት ቢውል በእመቤቲቱ አፍ
ከእመቤትስ በላይ ሹምስ ማንን ያምናል
በሃጥዕ ዘመን ዘንድ ጻድቅ ወህኒ ይወርዳል
ምንም ቢያልፍ ተሳቆ በሚያልፍ ባለ ጊዜ
በማያልፍ ተጥሷል ደርሶ የእውነት ጊዜ
በአደባባይ ቢያፍር እውነትን አነግሶ
ክብሩም በአደባባይ ይሄው ተመልሶ

ሃብት ነው ጌጥ እውነት ምን ባይሆን ለጊዜው
ከርሞም ቢመነዘግ ከፋይ ለከፈለው

እውነትን በተቀማ ትውልድ
ማን ይሆን የእውነት ዘመድ
ብርሃን ቃሉን ሲሰጥ ጨለማን ሲደክመው
የእውነት ቤት ይደምቃል
ለእግዚአብሔር ያደረው

ጽኑ ጽኑ ጽኑ ጽኑ ጽኑ ጽኑ X2
እውነት እግዚአብሔር ነው የማይለወጥ ጽኑ
በሰልፍ ብዛት የማይደክመው ከበረታው በላይ ብርቱ
ባህርይው ሰላም ነው አያምንም በሁከት
ራሱን ለማሳመን አይገባም ከጭንቀት
ህሊና ወዳጁ ጊዜ መፍቻ ቁልፍ
ተረጋግቶ ይኖራል ተከፍቶ በስንቱ
 
  ጽኑ ጽኑ