From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ሀና ተክሌ (Hana Tekle)
|
|
፲ (10)
|
አልበም (3)
|
ቁጥር (Track):
|
፲ (10)
|
ርዝመት (Len.):
|
5
|
ጸሐፊ (Writer):
|
ግሩም ምትኩ (GirumProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የሀና ተክሌ ፡ አልበሞች (Albums by Hana Tekle)
|
|
ባርኮቴ ብዙ ነዉ-የተደረገልኝ ስንቱ ነው
በረከቴን እቆጥራለሁ-የተደረገልኝ ብዙ ነው
እግዚአብሔር ይመስገን (8*)
አምና ላይ ደረስኩኝ ካቻምናን ዘግቼ
ዘንድሮን ደግሞ አየሁ አምናን ረስቼ
ከማላየው ክፋት በክንፉ ሸሽጎኝ
ከማላውቀው ጥፋት በድንቅ አስመልጦኝ
እኔ አለሁኝ
በእርሱ ምህረት በእርሱ ደግነት (3*)
እኔ አለሁኝ
ዛሬ ሰላም ነው ቤቴ
ተጠብቆ በአባቴ
እንደቀልድ "ደህና ነሽ ወይ ?" ቢሉኝ
እግዚአብሔር ይመስገን አልኩኝ
እግዚአብሔር ይመስገን(2*)
መድሃኔዓለም ይክበር
አባቴ ይመስገን
የምልበት ብዙ አለኝ (4*)
የሰራው ሰማይን ያበጀው ምድርን
እግዚአብሔር አይደለም ወይ
አመላኬ አይደለም ወይ
ባበጀው ምድር ላይ
የሚያኖረው ህዝቡን እኔን
እግዚአብሔር አይደለም ወይ
አምላኬ አይደለም ወይ
መውጣት መግባቴ በእኔ አይደለም
ሰላም ውሎ ማደሬ ቀልድ አይደለም
ጤናዬን ሰላሜን እርሱ ይዞት እንጂ
ጠላት መች ዘንግቶ የእኔን ደጅ
ቀን ይመሻል ይነጋል እያየሁት
ክረምት በጋውንም ይኸው ለመድኩት
ትላንት ዛሬንም ያየሁት በእርሱ ነው
ያለተነካሁት ምክንያቱ እግዚአብሔር ነው
በደግነቱ እኔን ያኖረኛል
በቸርነቱ እኔ ያቆመኛል
በደግነቱ እኔን ያኖረኛል
በቸርነቱ እኔን ያቆመኛል
በእርሱ ምህረት በእርሱ ደግነት (2*)
አመታቶቹ የርሱ ናቸው
በቸርነቱ የሚያቀዳጀው
በሆነው ባላሆነው
ልቤን አላዝልም
እግዚአብሔር ይመስገን
ለነገም አልተክዝም
እግዚአብሔር ይመስገን!
|