በታሪክህ (Betarikeh) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 3.jpg


(3)

አልበም
(Habtesemay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2020)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ክቡር የሰው ልጅ፣
ክቡር በሰማይ በምድር፣
የአንድ ዘር ቅጂ፣ የአንድ ዘር እፍን፣
አሻራ መልኩ ቢለያይ ቀለሙ
ወርቁ ቢፈተሽ አንድ ነው ደሙ

ከጎሳ ከዘር፣ ከባህል ትውፊት
ከሀገርም በላይ ከብሄር በፊት
አብ የፈጠረው በሁሉ አንግሶ
ወልድ የሞተለት ደሙን አፍስሶ

ሰው ነው ክቡር ሰው
የተከበረ
ባምሳለ እግዚአቤር የተመተረ
ምኑም ቢለያይ ድንበር አብሶ
አንድ አድርጎታል ክርስቶስ ሞቶ

ክቡር ክቡር ክቡር
ክቡር ክቡር ክቡር
ክቡር ክቡር ክቡር ፍጡር
ክቡር ክቡር ክቡር

በታሪክ፣ ማይገናኘውን
በታሪክ፣ ልዩነት ያለውን
የዘር የዳድ፣ ድንበር ያበጀውን
በምንም በምንም፣ ጭራሽ ማይገጥመውን

እየሱስ፣ በታሪክህ አንድ አደረግከው
በታሪክህ፣ አገናኘኸው
በመስቀልህ፣ አንድ አደረግከው
በታሪክህ፣ አገናኘኸው

አንድ ነን ማለት ይቻለ፣
ከኔ በላይ ላሳር ያለ፣
ክርስቶስ በመስቀል፣ የስንቱ ልብ ተቀየረ፤
ምሳሌ የሆከው ለፍቅር፣
አሳየኸው ዝቅን ማለት፣
የእግዚአብሄር ልጅ ሆነህ ሳለህ፣
ፈቅደህ መከፋትህን፣
አሳየሀው የፍቅርን ልብ፣
እኔነቱን አስወገድከው፣
በታሪክህ አሸንፈህ፣
ታሪኩን ከንቱ አደረግከው፤

በታሪክህ አንድ አደረግከው፣
በመስቀልህ አገናኘኸው፤

ጨዋ የለም፣
ባርያ የለም፣

ጉራማይሌውን፣ አንድ አደረግክ፣
ማይገናኘውን፣ አገናኘህ፣
ህዝብህ ልጅ፣ አንተ አባት ተባል፣
ህዝብህ ልጅ፣ አንተ አብ አባት ተባል፤
x 3

በታሪክህ x 2
በመስቅልህ x 2