From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ኃያል ፡ ሥም ፡ አለው
በዚህ ፡ ሥም ፡ አምነን ፡ ድነናል ፡ ይኸው
ምስክሮቹ ፡ ነን ፡ ሕይወት ፡ ደርሶናል
ሰማይ ፡ ሲጎበኘን ፡ ለዓለም ፡ በርተናል
ተጠቅልለናል ፡ በክርስቶስ ፡ በኃያሉ ፡ ሥም
ከነበርንበት ፡ ዓለም ፡ የለንም
የሚበልጥ ፡ አይተን ፡ የሚደንቅ ፡ ክብር
ሰውን ፡ ኑ ፡ እንላለን ፡ አልፈን ፡ ከምድር
አምላክ ፡ ሥጋ ፡ ሆነ ፡ ለእኛ ፡ ማለደ
ከአብ ፡ አስታረቀን ፡ ስርየት ፡ ወረደ
ሕያው ፡ ልጆቹ ፡ ነን ፡ ዳግም ፡ ወልዶናል
ዘላለም ፡ ሲያገኘን ፡ ከሞት ፡ ጠፍተናል
ተጠቅልለናል ፡ በክርስቶስ ፡ በኃያሉ ፡ ሥም
ከነበርንበት ፡ ዓለም ፡ የለንም
የሚበልጥ ፡ አይተን ፡ የሚደንቅ ፡ ክብር
ሰውን ፡ ኑ ፡ እንላለን ፡ አልፈን ፡ ከምድር
እናንት ፡ መኳንንቶች ፡ በሩን ፡ ክፈቱ
የክብር ፡ ንጉሥ ፡ ይግባ ፡ በሩን ፡ ክፈቱ
ይሄ ፡ ንጉሥ ፡ ማነው ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
የክብር ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)
እርሱ ፡ እግዚአብሔር
የክብር ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ የክብር ፡ ሁሉ ፡ ገዢ
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ኃያል (፪x)
የሰማይ ፡ የምድሩ ፡ የልዑላን ፡ ጌታ
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ኃያል (፪x)
ሆሆ ፡ ኃያሉ ፡ እግዚአብሔር
እርሱ ፡ እኛን ፡ ጎበኘ
እንድንዘምርለት ፡ ዙሪያው ፡ ሰበሰበን
ሆሆ ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን
እግዚአብሔር ፡ አሰበን
በየደረስንበት ፡ ኃያል ፡ መዝሙር ፡ ሆነን
ምሥጋና ፡ የተገባው ፡ እርሱ ፡ ነው
ውዳሴ ፡ የተገባው ፡ እርሱ ፡ ነው
ለእኛ ፡ ታየን ፡ መድኃኔዓለም
እንደርሱ ፡ የለም ፡ ዘላለም
ለእኛ ፡ ተገለጠ ፡ መድኃኔዓለም
እንደርሱ ፡ የለም ፡ ዘላለም
ዝማሬ ፡ የተገባው ፡ እርሱ ፡ ነው
ስግደትም ፡ የተገባው ፡ እርሱ ፡ ነው
ለእኛ ፡ ታየን ፡ መድኃኔዓለም
እንደርሱ ፡ የለም ፡ ዘላለም
ለእኛ ፡ ተገለጠ ፡ መድኃኒዓለም
እንደሱ ፡ የለም ፡ ዘላለም
|