From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አንደበት ፡ ይታክታል
የሆድን ፡ ሁሉ ፡ ቢናገር
ለመጣው ፡ ለሄደው ፡ ሁሉ
የሚያልፍበትን ፡ ቢዘረዝር
የሰሚም- ፡ የሰሚም ፡ ጆሮ ፡ ይዝላል
ለጊዜው ፡ ለሰሞንም ፡ ቢያዝን
ብቻ ፡ ልቤን ፡ ደግፈው
አልፈዋለው ፡ ብርቱውን ፡ ቀን
ብቻ ፡ ልቤን ፡ ደግፈው
አልፈዋለሁ ፡ ክፍውን ፡ ቀን
እጠራሃለሁ
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ ሰላም ፡ አለ
እጠራሃለሁ
በስምህ ፡ ውስጥ ፡ ብርታት ፡ አለ
በስምህ ፡ ውስጥ
እግዚአብሔር
አዝ፦ በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ ሰላም ፡ አለ
በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ እረፍት ፡ አለ
በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ ጽናት ፡ አለ
በሥምህ ፡ ውስጥ
ከፀሓይ ፡ በታች ፡ መልስ ፡ ባጣሁለት ፡ ጉዳይ
ቢያይልም ፡ ግርታዬ ፡ አይኔን ፡ ተክያልህ ፡ ሰማይ
ከያዘኝ ፡ ከከበበኝ ፡ በላም ፡ አንተን ፡ አምንሃለሁ
ብቻ ፡ ልቤን ፡ ደግፈው
አልፈዋለው ፡ ብርቱውን ፡ ቀን
ብቻ ፡ ልቤን ፡ ደግፈው
አልፈዋለሁ ፡ ክፍውን ፡ ቀን
ልቤ ፡ ተጠብቆ ፡ በሚሆነው ፡ ነገር
እታገስሃለሁ ፡ አለህ ፡ አንድ ፡ ነገር
ብቻ ፡ ልቤን ፡ ጠብቀው
አልፈዋለው ፡ ብርቱውን ፡ ቀን
ብቻ ፡ ልቤን ፡ ደግፈው
አልፈዋለሁ ፡ ክፍውን ፡ ቀን
አዝ፦ በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ ሰላም ፡ አለ
በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ እረፍት ፡ አለ
በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ ጽናት ፡ አለ
በሥምህ ፡ ውስጥ
ልብ ፡ ብቻውን ፡ ሲቀር ፡ በሃሳብ ፡ ሲወረር
በሁነኛ ፡ ነፋስ ፡ በማዕበል ፡ ሲሰወር
ደጋፊ ፡ ከሌለው ፡ ማን ፡ ከማን ፡ ያስጣል
ልብ ፡ የወደቀ ፡ ቀን ፡ ለሞት ፡ እጅ ፡ ያሰጣል
ልቤን ፡ የሚታደግ ፡ ብርቱ ፡ ግንብ ፡ አለቴ
አጥር ፡ ሃይሌ ፡ ስምህ ፡ ነው ፡ የተስፋ ፡ ጽናቴ
አንተ ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጽኑ ፡ መታመኛ
አደራ ፡ የምለው ፡ አንተን ፡ ነው ፡ የልቤን ፡ መገኛ
አዝ፦ በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ ሰላም ፡ አለ
በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ እረፍት ፡ አለ
በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ ጽናት ፡ አለ
በሥምህ ፡ ውስጥ
|