ካህን (Kahin) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 3.jpg


(3)

ሃብተ ፡ ሰማይ
(Habete Semay)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ካህን በገዛ ደምህ አዳንከኝ
ካህን በገዛ ቁስልህ አተረፍከኝ
ከፍለህ አቋደስከኝ ህይወትህን
ቆርሰህ አካፈልከኝ ነፍስህን
ከዚህ የጨመረ ምን ፍቅር ይኖራል
ከዚህ ደርዝ ያለፈ ምን መውደድ ይገኛል
መስዋዕት ከመሆን ከመሞት የባሰ
ለነፍስ ነፍስ ከማጣት ከማለፍ ያለፈ
ብልህ የመውደድ ልክ የፍቅር ዳርቻ
ህይወቴ ተገኝቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
በክርስቶስ ብቻ
ህይወቴ ተርፎልኝ ባንተ ፍቅር ብቻ
ጨለማዬ በርቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
በክርስቶስ ብቻ
በስቃይህ ብቻ
በህማምህ ብቻ

ልታድነኝ ልታተርፈኝ ወደህ ይሄድክበት
የሞትህ ነው ያልተገባህ በደም ያለፍክበት
ከሞትም የስቃይ በእንጨት ተንጠልጥለህ
ጻድቅ ያለሃጥያትህ ከአባይ መሃል ውለህ
ቅን ደጉ ታመምህ የዋህ ስቃይ ገባህ
ፍቅር ተገደልህ ህይወቴ እንዲገባ
ብልህ የመውደድ ጥግ የፍቅር ዳርቻ
ህይወቴ ተርፎልኝ ባንተ ፍቅር ብቻ
ጨለማዬ በርቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
በክርስቶስ ብቻ
በስቃይህ ብቻ
በህማምህ ብቻ