ሁሉን ፡ በስርህ (Hulun Besirih) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 3.jpg


(3)

ሃብተ ፡ ሰማይ
(Habete Semay)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:10
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ፊደል ተገጣጥሞ የቱ ቃል ገለጠህ
ቃላት ተሰካክተው ምን ቢባል ተረከህ
ያንተን ልክ አዋቂ አንተ እግዚአብሄር ብቻ
ራስህ ንገረኝ ምን እንድልህ ብቻ
የተባልከው ሁሉ ካንተ በታች ሆኗል
ለፍጥረት ሚበዛ ላንተ አቅም አንሶታል
ያንተን ልክ አዋቂ አንተ እግዚአብሄር ብቻ
ራስህ ንገረኝ ምን እንድልህ ብቻ

መጀመሪያም መጨረሻም የሌለህ
አልፋ ኦሜጋ ፊተኛም ኋለኛም የሌለህ
እግዚያብሄር አንተ ነህ
እግዚያብሄር አንተ ነህ
የኔ ትልቅ አንተ ነህ
የኔ ጀግና አንተ ነህ
ሁሉን በስርህ አስተዳዳሪ
በላይ ለሁሉ ሁሉን ፈጣሪ
የግዙፍ ግዙፍ የትልቅ ትልቅ
ቃል በማይደፍረው የከፍታ ጥግ
አንተ እግዚአብሄር አንተ ብቻ ነህ
ትልቅ መሳዩን ትንሽ ያረግህ
ጀግና መሳዩን ያንበረከክህ
ጠቢብ መሳዩን ሞኝ ያደረግህ
ያለው መሳዩን ባዶ ያደረግህ

የለም ያሉህ የሉም
ዛሬም የሚሉህ ነገ አይኖሩም
ይገርመኛል ትጋታቸው
ለከንቱነት ጥበባቸው
ካንተ ውጪን ህይወት ማሰባቸው
አንተ ባበጀኸው አእምሮ
ባንተው ጥበብ ተቀምሮ
እስትንፋስ ሰጥተኸው በእፍታህ
በአምሳልህ ቀርጸኸው ስታበቃ
የለህም የሚልህ ማነው???
እኮ የለህም የሚልህ ማነው???
ለመኖርህ የእሱም መኖር ምስክር ነው
ለመኖርህ የእሱም መኖር ምስክር ነው
ለመኖርህ የእሱም መኖር ምስክር ነው
ለመኖርህ የእኔም መኖር ምስክር ነው

ሉዐላዊነትህ ከጥንት ከአለማት በፊት የነበረ
አለህም የለህም ቢባል ከመኖር ያልተገደበ
እግዚአብሄር አለህ በማደርያህ
እግዚአብሄር አለህ በዙፋንህ
እግዚአብሄር አለህ በማደርያህ
እግዚአብሄር አለህ በዙፋንህ
አለህ በማደርያህ አለህ
አለህ በዙፋንህ አለህ
አለህ በማደርያህ አለህ
አለህ በዙፋንህ አለህ
ኧረ አለህ በማደሪያህ አለህ