ሃብተ ፡ ሰማይ (Habte Semay) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 3.jpg


(3)

ሃብተ ፡ ሰማይ
(Habete Semay)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

አዲስ ሰማይ አዲስ ምድር
የብርሃን ሀገር የብርሃን ቅጥር
ምዕራፍ ተዘግቶ ምዕራፍ ሲጀመር
አየዋለዉ ያኔ በድል በክብር
     ሲያልፍ ፌተኛዉ ሰማይ
     ደግሞ እንደገና አዲስ ሰማይ
     ሲያበቂ ይህኛዉ ምድር
     ዘላለም አለ የክብር ምድር
ጨለማ ዳግም በማሰፍንበት
ፀሀይም ጨረቃም በሌሉበት
በጉ ብርሀን ነዉ ያበራል
ሀገር በክርስቶስ ይደምቃል
     ሀብተ ሰማይ ፅኑ ተስፋዬ
     ከኢየሱስ ጋር የዘላለም መኖሪያዬ
     ሀብተ ሰማይ ፅኑ ተስፋዬ
     ከኢየሱስ ጋር ለዘላለም መንገሻዬ
አይን ያላየዉ ጆሮም ያልሰማዉ
ጌታ ለሚወዱት ያዘጋጀዉ
ልብሳቸዉን በበጉ ደም ላጠቡ
የሰፋዉን መንገድ ጥለዉ ለዘለቁ
     ሀብተ ሰማይ ፅኑ ተስፋዬ
     ከኢየሱስ ጋር የዘላለም መኖሪያዬ
     ሀብተ ሰማይ የክብር ተስፋዬ
     ከኢየሱስ ጋር ለዘላለም መንገሻዬ
በተስፋ እንድንኖር በፍቅር ሀገር
የእምነት ፆናት ምላሽ ሲሰምር
ሲበሰር የዘላለም ሙሉ ደስታ
የታመኑት የናፈቁት ለሀይን ሲበቃ
     ሀብተ ሰማይ ፃኑ ተስፋዬ
     ከኢየሱስ ጋር የዘላለም መኖሪያዬ
     ሀብተ ሰማይ የክብር ተስፋዬ
     ከኢየሱስ ጋር ለዘላለም መንገሻዬ
ሌት በማያዉቀዉ የቀን ጅረት
ብርሃን ዉሎ ብርሃን ማደር
ምን አለ ደስታ ምን አለ ዉበት
ከክርስቶስ ጋር ነግሶ እንደ ማየት
ሞት በማይገጥመዉ የሕይወት ጅረት
ድል ከነሱት ጋር ተካፍሎ ርስት
ምን አለ ዉበት ምን አለ ፍስሃ
እንደመገኘት ከዚ ክብር ጋር
     ሲያልፍ ፌተኛዉ ሰማይ
     ደግሞ እንደገና አዲስ ሰማይ
     ሲያበቂ ይህኛዉ ምድር
     ዘላለም አለ የክብር ምድር