ይቅር ፡ በለን (Yeqer Belen) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 1.jpg


(1)

አግዘኝ
(Agezegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ሰው ፡ መሆኑን ፡ አይደል ፡ ልብሱን ፡ አከበረ
ሰው ፡ በገንዘቡ ፡ ልክ ፡ ወዳጅ ፡ አስቆጠረ (አቤት ፡ አቤት)
ምስኪኑ ፡ ሲመጣ ፡ አጥቶ ፡ የሚቀምሰው
የሚቀርበው ፡ ጠፍቶ ፡ ፍቅር ፡ እንኳን ፡ ከራቀው
አቤት ፡ አቤት ፡ አቤቱ ፡ ምን ፡ አልከው

አዝአቤቱ ፡ አትታዘበን
እንመለሳለን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x)
ምሕረቱን ፡ ተማምነን ፡ አይተን ፡ እንደዋዛ
የድፍረታችን ፡ ልክ ፡ ሃጥያታችን ፡ በዛ
ታጋሽ ፡ ሳይፈርድብን ፡ ቁጣውን ፡ ሳይልከው
ይብቃን ፡ እንመለስ ፡ ዝምታው ፡ ምክር ፡ ነው

የቤትህ ፡ አገልጋይ ፡ ስንቱን ፡ ሕዝብ ፡ አሰረው
የሚያወራው ፡ አፉ ፡ ልቡ ፡ ግን ፡ ሌላ ፡ ነው (አቤት ፡ አቤት)
ተግባር ፡ የለሽ ፡ ምክሩ ፡ ለራሱም ፡ ካልበጀው
ልጅ ፡ አባቱ ፡ ታሞ ፡ እንዴት ፡ ይመልሰው
አቤት ፡ አቤት ፡ አቤቱ ፡ ምን ፡ አልከው

አዝ፦ አቤቱ ፡ አትታዘበን
እንመለሳለን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x)

ያከበርከው ፡ ትዳር ፡ ያቀናኸው ፡ ጎጆ
ሊዘልበት ፡ ጠላት ፡ ተንዶ ፡ ተንዶ (አቤት ፡ አቤት)
እንደ ፡ አሸዋ ፡ ሲርድ ፡ ከአለት ፡ ያፀናኸው
እሌላ ፡ ሲከጅል ፡ በክብር ፡ የዳርከው
አቤት ፡ አቤት ፡ አቤቱ ፡ ምን ፡ አልከው

ምሕረቱን ፡ ተማምነን ፡ አይተን ፡ እንደዋዛ
የድፍረታችን ፡ ልክ ፡ ሃጥያታችን ፡ በዛ
ታጋሽ ፡ ሳይፈርድብን ፡ ቁጣውን ፡ ሳይልከው
ይብቃን ፡ እንመለስ ፡ ዝምታው ፡ ምክር ፡ ነው

መስሎት ፡ የተማረ ፡ በልጦበት ፡ እውቀቱ
አምላክ ፡ የለም ፡ አለኝ ፡ ኢኸው ፡ እንደልቡ ፡ ይህ ፡ ሰው (አቤት ፡ አቤት)
የአመፃው ፡ ብዛት ፡ ሃጥያቱም ፡ ሲከፋ
ሴት ፡ ለሴት ፡ ተዳረች ፡ ወንድም ፡ ወንድ ፡ አገባ
አቤት ፡ አቤት ፡ አቤቱ ፡ ምን ፡ አልከው

አዝ፦ አቤቱ ፡ አትታዘበን
እንመለሳለን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x)

ለተመቸው ፡ እርሙ ፡ መች ፡ ይቅርታን ፡ ያውቃል
ይልቅ ፡ ለጥፋቱ ፡ ጥቅስ ፡ ይሸራርፋል ፡ ይህ ፡ ሰው ፡ አቤት ፡ አቤት
መውጣቱስ ፡ ይክበደው ፡ አጠፋሁ ፡ ቢል ፡ ምነው
እራስን ፡ አታሎ ፡ መጨረሻው ፡ የት ፡ ነው
አቤት ፡ አቤት ፡ አቤቱ ፡ ምን ፡ አልከው

ምሕረቱን ፡ ተማምነን ፡ አይተን ፡ እንደዋዛ
የድፍረታችን ፡ ልክ ፡ ሃጥያታችን ፡ በዛ
ታጋሽ ፡ ሳይፈርድብን ፡ ቁጣውን ፡ ሳይልከው
ይብቃን ፡ እንመለስ ፡ ዝምታው ፡ ምክር ፡ ነው