ወንጌል ፡ ሰላም (Wengiel Selam) - ሃና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሃና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 1.jpg


(1)

አግዘኝ
(Agezegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

 
ይህን ፡ ነገር ፡ ለዓለም ፡ ቅዱሱ ፡ መጽሃፍ
ከዳር ፡ ዳር ፡ ሰማሁ ፡ እውነቱ ፡ አይታለፍ
ዘር ፡ ቀለም ፡ ላይለየው ፡ ለሁሉም ፡ ተፈቅዷል
ለወደዱት ፡ ሁሉ ፡ ሰላምን ፡ ይሰጣል

አዝ:- ወንጌል ፡ መሪ ፡ ወንጌል ፡ ሰላም
ለሰው ፡ ልጆች ፡ ይሁን ፡ መዳን
ለህዝባችን ፡ ይሁን ፡ መዳን (፪x)
የታሰሩ ፡ ይፈታሉ ፡ የታመሙት ፡ ይድናሉ
ይፈታሉ ፡ ይድናሉ ፡ ፈውስ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ
(ኡዎዉዎዎ) ፈውስ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ ፡ ፈውስ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ (፪x)

ሊታረም ፡ የማይችል ፡ ፍፁም ፡ እውነት ፡ አለው
ሊሽረው ፡ የቆመ ፡ የትኛው ፡ ጠቢብ ፡ ነው
የጠቢባን ፡ ጠቢብ ፡ ይህን ፡ ከገለጸው
የደህንነት ፡ መንገድ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝ:- ወንጌል ፡ መሪ ፡ ወንጌል ፡ ሰላም
ለሰው ፡ ልጆች ፡ ይሁን ፡ መዳን
ለህዝባችን ፡ ይሁን ፡ መዳን (፪x)
የታሰሩ ፡ ይፈታሉ ፡ የታመሙት ፡ ይድናሉ
ይፈታሉ ፡ ይድናሉ ፡ ፈውስ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ
(ኡዎዉዎዎ) ፈውስ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ ፡ ፈውስ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ (፪x)