ሞትክልኝ ፡ መድህኔ (Motkelegn Medhenie) - ሃና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሃና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 1.jpg


(1)

አግዘኝ
(Agezegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

 
ስፍራን ፡ አዘጋጅተህ ፡ እኔን ፡ ከጠራኀኝ
በክብር ፡ እንድኖር ፡ ወደኅኝ ፡ ከአዳንከኝ
ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ቀርበኀኛልና
ውዴ ፡ ተቀበለኝ ፡ የልቤን ፡ ምሥጋና

አዝ:- በዋጋ ፡ ገዝተኀኛል ፡ ከእንግዲህ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል
የዚች ፡ ምድር ፡ አይደለሁምና
በስምህ ፡ ላብዛልህ ፡ ምሥጋና
በደሌን ፡ ሽረሃል ፡ እኔን ፡ ግን ፡ ወደሃል
ሞቴን ፡ ወስደህ ፡ ከእኔ ፡ ሞትክልኝ ፡ መድህኔ
(፪x)

የዳነን ፡ ማንነት ፡ ከአንተ ፡ አግኝቻለሁ
ሥጋቴን ፡ ጭንቀቴን ፡ ለአንተው ፡ ትቼዋለሁ
ፍፁም ፡ ሰላም ፡ በአንተ ፡ ከአንተ ፡ ሆኖልኛል
ለዘለዓለም ፡ መኖር ፡ መብቱ ፡ ተሰጥቶኛል

አዝ:- በዋጋ ፡ ገዝተኀኛል ፡ ከእንግዲህ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል
የዚች ፡ ምድር ፡ አይደለሁምና
በስምህ ፡ ላብዛልህ ፡ ምሥጋና
በደሌን ፡ ሽረሃል ፡ እኔን ፡ ግን ፡ ወደሃል
ሞቴን ፡ ወስደህ ፡ ከእኔ ፡ ሞትክልኝ ፡ መድህኔ
(፪x)

የፈሰሰልኝ ፡ ደም ፡ በእውነት ፡ ደምህ ፡ ነው
ሕይወት ፡ የሆነልኝ ፡ ሙት ፡ ለነበርኩት ፡ ሰው
እንዳልጠፋ ፡ አድርገህ ፡ አንተ ፡ አድነኀኛል
ላደረክልኝ ፡ ሁሉ ፡ መልሴ ፡ ያንስብሃል

አዝ:- በዋጋ ፡ ገዝተኀኛል ፡ ከእንግዲህ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል
የዚች ፡ ምድር ፡ አይደለሁምና
በስምህ ፡ ላብዛልህ ፡ ምሥጋና
በደሌን ፡ ሽረሃል ፡ እኔን ፡ ግን ፡ ወደሃል
ሞቴን ፡ ወስደህ ፡ ከእኔ ፡ ሞትክልኝ ፡ መድህኔ
(፪x)