ምሳሌዬ (Mesalieyie) - ሃና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሃና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

Hana Tekle 1.jpg


(1)

አግዘኝ
(Agezegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

 
ምሳሌዬ ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ በምግባርህ ፡ የማውቅህ
ንግግርህ ፡ ከሩቅ ፡ ይጠራል ፡ ጨዋነትን ፡ ተላብሰሃል
ከውስጤ ፡ ገብተህ ፡ ቀርተሃል ፡ ማን ፡ ቢፈለግ ፡ ይተካሃል
ጥበብ ፡ ፍቅርም ፡ በአንተ ፡ ይለካል ፡ አዋቂነትስ ፡ ከአንተ ፡ ይቀዳል

አዝ:- አስተዋይ ፡ ወዳጄ ፡ ብልህ ፡ ብትገባኝ ፡ ነው ፡ ባውቅህ
ጠቢብ ፡ ብዬ ፡ ብጠራህ ፡ ቃል አጥቼ ፡ ለስምህ
ጻድቅ ፡ ፍፁም ፡ ነህ (፬x)

አለቅነት ፡ በአንተ ፡ ያምራል ፡ አስተዳደር ፡ በአንተ ፡ ይሰላል
መታገስህ ፡ ሁሉን ፡ ያልፋል ፡ መቼ ፡ ፍርድህ ፡ ቀድሞ ፡ ያውቃል
የሊቅ ፡ ጥጉ ፡ መደምደሚያ ፡ የትሁት ፡ ልብ ፡ ማሳረጊያ
ፍትህ ፡ ሚዛኑ ፡ በአንተ ፡ ከወጣ ፡ ዳኝነቱም ፡ ካንተ ፡ ይምጣ

አዝ:- አስተዋይ ፡ ወዳጄ ፡ ብልህ ፡ ብትገባኝ ፡ ነው ፡ ባውቅህ
ጠቢብ ፡ ብዬ ፡ ብጠራህ ፡ ቃል አጥቼ ፡ ለስምህ
ጻድቅ ፡ ፍፁም ፡ ነህ (፬x)

የሁሉን ፡ ከፍታ ፡ ይዘሃል ፡ ወርደህም ፡ አዳምን ፡ ሁነኃል
ከፍም ፡ ብለህ ፡ ዝቅም ፡ ብለህ ፡ ፍፁም ፡ ጌታ ፡ አንድ ፡ አንተ ፡ ነህ
ሁሉን ፡ በእኩል ፡ የምታየው ፡ ምስኪኑንም ፡ የማትንቀው
የደግነት ፡ መገለጫ ፡ የሁሉ ፡ አባት ፡ አንተ ፡ ብቻ

ውዴ ፡ ውበትህ ፡ ማንነትህ ፡ ደም ፡ ግባትህን
አይቼው ፡ አይቼው ፡ አልችልም ፡ ልገልጽህ (፬x)